Sunday, September 8, 2013

ጳጉሜ 4


በዚህች ቀን ተጋዳይ አባ ባይሞን አረፈ።ከስድስት ወንድሞቹ ጋር መንኖ ገዳመ አስቄጥስ ገባ በተጋድሎም ኖረ፤ በእውቀት ከሁሉም ይበልጥ ነበር ሽማግሌዎችንና ወጣት መነኮሳትን የሚያረጋጋ የሚያጸና ነበር ብዙ ድርሳናትን ተግሳጻትን ጽፏል። ደስ ከሚሉ ትምህርቶቹ አንዱ "የተሰነካከለ ወንድምህን ብታይ ስለርሱ ተስፋ አትቁረጥ ልቡን አንቃለት እንጂ ከወደቀበትም እንዲነሰ አጽናንተህ ሸክሙን አቅልልለት"። "አፍህ የተናገረውን ይሰራ ዘንድ ልብህን አስተምረው" ይህ አባት እስከ ሽበት እስከ ሽምግልና በትሩፋት በተጋድሎ ኖሮ በዛሬዋ ቀን በክብር አረፈ በረከቱ ይደርብን።

LIKE >>>

https://www.facebook.com/pages/ተዋህዶ-ሀይማኖታችን/117298008428339?ref=hl

No comments:

Post a Comment