Monday, September 2, 2013

ነሐሴ 27በዚህች ቀን ከሰባቱ ሊቃነ መላአክት አራተኛ የሆነው የመለአክት አለቃ የቅዱስ ሱርያል የበዓሉ መታሰቢያ ነው። እግዚያብሔር መፍጠር በጀመረበት እሁድ በ 9ኛው ሰዓት ቅዱስ ሱርያልን ስልጣናት በሚባሉ የመላአክት ነገድ ላይ አለቃ አድርጎ ሾሞታል። ይህ መለአክ ነገዱን ይዞ በራማ ነው የሚገኘው፤ ራማ ሁለተኛው የመላክት ከተማ ነው ቅዱስ ገብርኤልም እዚህ ነው የሚገኘው። አንደኛው የመላአክት ከተማ ኢዮር ነው የስላሴን መንጦላእት የሚከፍትና የሚዘጋው ቅዱስ ሚካኤል እነዲሁም ዙፋኑን የሚሸከሙ ኪሩቤልና ሱራፌል ያሉበት ከተማ፤ 3ኛው የመላክት ከተማ ኤረር ነው በዚህም 3 የመላክት ነገዶች አሉ።የቅዱስ ሱርያል አማላጅነቱ አይለየን። የነሐሴ 27 ስንክሳር፤ መጽሐፈ አክሲማሮስ

No comments:

Post a Comment