Sunday, September 8, 2013

ጳጉሜ 2


በዚህች ቀን ሐዋርያው ጳውሎስ መልዕክት የጻፈለት የከበረ ሐዋርያ ቲቶ አረፈ።የዚህ ቅዱስ አጎቱ የአክራጥስ አገር ገዥ ነበር፡፡ በዚያን ወራት የጌታችን ትምህርት ተአምራቱ በብዙ አገሮች ተሰምቶ ነበርና ይህንን እንዲያጣራ መኮንኑ ቲቶን ይልከዋል እርሱም ወደ ይሁዳ ምድር እየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ የጌታችንን ህይወት የሚሰጥ የቃሉን ትምህርት የእጁን ተአምራት አይቶ ተከተለው ጌታም ተቀብሎ ከ 72ቱ አርድእት ቆጠረው፤ ከእርገቱ በኃላ መንፈስ ቅዱስን ተቀበለ፤ከዚያም ቅዱስ ጳውሎስን እየተከተለ ወንጌልን ሰበከ ቅዱስ ጳውሎስ ሮም በሰማእትነት ከሞተ በኃላ ወደ አክራጥስ ተመለሰ ቤተክርስቲያን አነጸ ቀሳውስት ዲያቆናትን ሾመ ህዝቡን እያስተማረ ኖሮ ጳጉሜ በባተ በሁለተኛው ቀን ወደ ወደደው ወደ እግዚያብሔር ሄደ።በረከቱ ይደርብን

LIKE >>> https://www.facebook.com/pages/ተዋህዶ-ሀይማኖታችን/117298008428339?ref=hl

No comments:

Post a Comment