Tuesday, September 17, 2013

መስከረም 8


በዚህች ቀን የነቢያት አለቃ የሆነ የዋህ፤ቅን፤ጻድቅ ሙሴ መታሰቢያው ነው። ከእግዚያብሔር ጋር 570 ቃላትን ተነጋግሯል፤ ከባለሟልነቱ የተነሳ ከዕለታት በአንዱ ቀን እግዚያብሔርን መቼ ነው የምሞተው ብሎ ይጠይቀዋል፤ ዐርብ ቀን ነው ብሎ ይመልስለታ ሙሴም ዐርብ ቀን ሁሌም ራሱን ገንዞ ተዘጋጅቶ ይጠብቃል ሰባት ዓመት አለፈው፤ ከዛ በኃላ ቀኑን ረሳው መዘጋጀቱንም ተወው፤ ነገር ግን ዐርብ ቀን ሁለት መላዕክት በሰው ተመስለው መቃብር ሲቆፍሩ አገኛቸው ምን እየሰራችሁ ነው አላቸው፤ እነሱም ሰው ሞቶብን መቃብር እየቆፈርን ነው አሉት፤ ላግዛችሁ ብሎ ቆፈረላቸው፤ እነሱም የሞተው ሰው አንተን ነው የሚያህለው ውስጥ ግባና ለካልን ይሉታል እርሱም ውስጥ ገብቶ በጀርባው ጋደም አለ ጣር ሳይኖርበት ህማም ሳይሰማው በዛው አሸለበ መላእክት አፈር አልብሰውት ያርጋሉ፤የሙሴ መቃብር እሰካሁን የት እንዳለ አይታወቅም፤ ምነዋ ቢባል እስራኤል በጣም ይወዱት ነበርና ስጋውን እንዳያመልኩት ነው። እንደ ሙሴ ደግ የዋህ ቅን የሆነ ነቢይ እንዳልተነሳና እንደማይነሳ መጽሐፍ በእውነት መሰከረ። ፍቅር እንደ ሙሴ ቸርነት እንደ አብርሃም ጥበብን እንደ ሰሎሞን ስጠን አይደል የምንለው። በረከቱን ያድለን

No comments:

Post a Comment