Thursday, September 5, 2013

ጳጉሜ 1እነሆ የጳጉሜ ወር ባተ ለእግዚያብሔር ምስጋና ይሁን፤ በዚህች ቀን የወንጌላዊው ዮሐንስ ረድእ ሐዋርያና ሰማዕት የከበረ ዑቲኮስ አረፈ። ይህ አባት በአረማውያን መካከል ወንጌልን ሰበከ ብዙዎችንም መለሰ፤ጣኦታትን አፈራረሰ፤ቤተክርስቲያኖችን አሳነጸ፤ በዚህም ብዙ መከራ ተቀበለ ታሰረ ለአንበሳ ተጣለ እሳት ውስጥ ተወረወረ፤ ከዚህ ሁሉ ግን የእግዚያብሔር መልአክ አዳነው እየመራም ወደ ቁስጥንጥንያ አገር ወሰደው በዚያም ወንጌልን ሲያስተምር ቆይቶ በበጎ ሽምግልና ጳጉሜ 1 በዛሬዋ ቀን አረፈ። በረከቱ ይደርብን።

No comments:

Post a Comment