Thursday, September 12, 2013

የቅድስት ድንግል ማርያም ክብር



የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ክብር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በጥቂቱ
ቅድስተ ቅዱሳን ትባላለች። በንጽሕና በቅድስና በክብር የተለየ ደረጃ አላት። ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በቤተክርስቲያን ምስጋና ይቀርብላታል መሠረቱም የእግዚአብሔር ቃል ነው። « ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ከሴቶች ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ። » ሉቃ 1፤28 « ከእግዚአብሔር ተልከው የነገሩሽን የምታምኚ አንቺ ብጽእት ነሽ። » ሉቃ 1፤45 በዚህ መሠረት ቤተ ክርስቲያን እመቤታችንን ብጽእት፤ ፍሥሕት፤ ቅድስት፤ ስብሕት እያለች ታመሰግናታለች። እሷ ራሷ « ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል» እንዳለች ሉቃ 1፤48 ዳዊትም « ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ» ብሏል መዝ 44፤17

እመቤታችን የማማለድ ሥልጣን አላት። እመቤታችን በእግዚአብሔር የተሰጣትን የአማላጅነት ክብር ክርስቲያኖች በማወቅ እመቤታችንን አማልጅን ለምኝልን እያሉ በፀሎት ስሟን ይጠራሉ ወደ እርሷ ይማልዳሉ « የምድር ባለጠጎች አሕዛብ በፊትሽ ይማልላሉ» መዝ 44፤13

መልአኩም እንዲህ አላት «በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስን አግኝተሻል» ሉቃ 1፤38 ሞገስ የሚለው ቃል ብዙ ጊዜ የሚያመለክተው የአማላጅነትን፤ የአስታራቂነትን፤ የባለሟልነትን መብት ነው። ሐዋ ሥራ 7፤45-46 ምልጃዋም በቃና ዘገሊላ ሰርግ ቤት ታይቷል። ዮሐ 2፤1-11

እመቤታችን ስግደት ይገባታል። ቤተ ክርስቲያን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የፀጋ (የአክብሮት) ስግደት እንዲቀርብ ታዛለች ለዚህም መሠረቱ የእግዚአብሔር ቃል ነው። « እግሮቹ በሚቆሙበት ቦታ እንሰግዳለን» መዝ 131፤7 ይህ ጥቅስ አራት ነገሮችን የሚያስተባብር ነው

1ኛ ኢየሩሳሌምን

2ኛ ቤተ ክርስቲያን

3ኛ መስቀልን

4ኛ እመቤታችንን

ለእመቤታችን እግዚአብሔር ሰው ሆኖ በእግሮቹ ምድርን ተመላልሶ ከመቀደሱ በፊት 9ወር ክ5ቀን በማህፀኗ 3 ዓመት ክ6ወር በጀርባዋ በእቅፏ ሆኖ ተመስግኖባታልና « ነገሥታትም አሳዳጊ አባቶች ይሆናሉ እቴጌዎቻችውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ ግንባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል» ኢሳ 49፤23

LIKE >>>
https://www.facebook.com/pages/ተዋህዶ-ሀይማኖታችን/117298008428339?ref=hl

No comments:

Post a Comment