Tuesday, September 10, 2013

እንካን አደረሰን



ከብረው ይቆዩን ከብረው

ልቡና መንፈስ ገዝተው

ቃሉን በትጋት ሰምተው

ሥጋና ደሙን በልተው

የፍቅርን ሸማ ለብሰው

ከብረው ይቆዩን ከብረው..

ቸርነቱና ምህረቱ በዘመናችን ሁሉ ይከተለን! እግዚአብሔርአምላክ በዘመናችን ሁሉ ማስተዋልና ጥበብን ይሥጠን! ዕድሜ ለንስሐ ዘመን ለፍስሐ ይስጠን! ዘመኑ የሠላም የጤና የምሀረት እና በሕይወታችን መልካም ፍሬ የምናፈራበት እንደፈቃዱ የልባችንን መሻት የምናገኝበት ይሆንልን ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን! አሜን! እግዚአብሔር ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር ሁላችንን ይባርክ! ይርዳን! ይጠብቀን!ከሁላችን ጋር ይሁን!አሜን! ሳይገባን እንደቸርነቱ ለዚህ ዕለት ለዚህ ዓመት ያደረሰን የእግዚአብሔር ስም ከእናቱ ከቅድስት ማርያም ጋር ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ ድረስ የተባረከ ይሁን! አሜን !መልካም አዲስ ዓመት!

እንካን አደረሰን!"ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምህረትከ ወይጸግቡ ጠላተ ገዳም"መዝ64:11"የምህረትህን ዓመት አክሊል ትባርካለች ምድረ በዳዎችም ጠልን ይጠግባሉ"መዝ64:11 በመጀመሪያይቱ የቅዱስ ጴጥሮስ መልዕክት ምዕራፍ4ቁ.3 "የአህዛብን ፈቃድ ዝሙት ስካርንና ወደቆ ማደርን ያለልክ መጠጣትና ጣኦት ማምለክን ያደረጋችሁበትን ያለፈው ዘመን ይበቃችኅልና እንግዲሀ ወደዚህ ሥራ እንዳትሮጡ ዕወቁ ከዚሀች ጎዳናና መጠን ከሌለው ከዚያ ሥራ ተለዩ:"እንደተባለው ከነዚያ ባለፈው ዘመን ስንገዛላቸው ከነበሩ ከስጋ ስራዎች እንለይ ዘንድ እናም በዚህ በአዲሱ ዓመት በቅድስና ሕይወት እንኖር ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን!እንዲሁም ልበ አምላክ ዳዊት በመዝ 26:4"እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔርቤት እኖር ዘንድእግዚአብሔርን ደስ የሚያሠኘውንም አይ ዘንድ በቤተ-መቅድሱም አገለግል ዘንድ ነው"ብሎ እንደተናገረው ለእኛ በቤቱ መኖርመልካምነውና በእርሱ ቤት እንኖር ዘንድ ደስ የሚያሰኘዉን ሥራ እንድንሠራ እግዚአብሔር ይርዳን!

አዲሱ ዘመን የሰላምና የጤና የስምምነት የንስሐ ዘመን ያድርግልን:: በየዓመቱ መስከረም 1 ቀን ብዙ ተደራራቢ እና ታላላቅ በዓላትን ነው አክብረን የምንውለው:: ቀዳሚው ዘመን መለወጫ;2.ሊቀ መላእክት ቅዱስ ራጉኤል በዓለ ሲመቱ ነው:: ራጉኤል ማለት መጋቤ ብርሃናት ማለት ነው; ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ነው:: ለሰው ልጅ ምህረትንና ቸርነትን የሚለምንና ዲያቢሎስን ከነሠራዊቱ የሚበቀል መልአክ ነው:: ሄኖ 6:3;::3.መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐን ከአምላኩ ዘንድ ለእኛ ድኅነት ይሆነን ዘንድ የማይታበል ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን የተቀበለበት::;
4.ጻድቁ ኢዮብ ከደረሰበት ፈተናና መከራ በእግዚአብሔር ቸርነት የተፈወሰበት ዕለት ነው::5. ከ 12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት መካከል አንዱ የሆነው ቅዱስ በርተሎሜዎስ ያረፈበት ዕለት ነው::በርተሎሜዎስ ማለት አትክልተኛ ማለት ነው:: ማቴ ሐዋ ሀገረ ስብከቱ አልዋህ ነው; በሚያስተምርበትም ጊዜ ብዙ ተአምራትን አድርጏል:. አንድ ቀንም በነግህ ወይን ተክሎ ዕለቱን ለመስዋዕት አድርሷል አትክልተኛ መባሉ ቅሉ ለዚህ ነው:: አምላካችን ከቅዱሳኑ ሁሉ ረድኤታቸውንና በረከታቸውን ያሳድርብን:: ለበለጠ መረጃ ሥንክሳር ዘመስከረም 1 እና መዝገ በታሪክ ቁጥር 1 ይመልከቱ::

መልካም አዲስ ዓመት!

No comments:

Post a Comment