Friday, March 8, 2013

የካቲት 30




"እውነት እላችኋለሁ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም፤" ማቴ 1111 ዛሬ የካቲት 30 የከበረች የመጥምቁ ዮሐንስ ራስ ተገለጸችበት ቀን ነው ሄሮድስ አንገቱን ለአንዲት ጋለሞታ ዘፈኝ ሲል አስቆረጠው፤ ማር 627 በዚህን ጊዜ ጣፋጭ መዓዛ አካባቢውን አወደው በዚህም ብዙ ድውያን ተፈወሱ ይላል። የተፍጻሚተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስን አንገቱን ሲቆርጡት ለሁለት ሰዓት አንገቱ አየር ላይ ቀጥ ብላ ቆመች ይላል፤ ግሩም ነው፤ ቅዱስ ጳውሎስ በጥላው ድውያን ይፈውስ ነበር፤ ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ በሰውነቱ መዓዛ የሚገርም ነው ከዚህ በኃላ በወጪት አድርጎ ለወለተ ሄሮዲያዳ ሰጣት የቅዱስ ...ዮሐንስ አንገት ክንፍ አውጥታ በረረች በደቡብ ዓረቢያ አስራ አምስት ዓመት ወንጌልን ሰበከች ሚያዚያ 15 ቀን አረፈች፤ ከዘመናት በኃላ ነጋዴዎች እዚያ ቦታ አደሩ ከነዚህም ሁለቱ ደጋግ ክርስቲያኖች ነበሩበት ቅዱስ ዮሐንስ በህልማቸው ተገለጸላቸው የከበረች እራሱንም እንዲያወጡ ነገራቸው ሲነጋም እንዳዘዛቸው አደረጉ ይህም የካቲት 30 ቀን ነው፤ ከቀሪ ስጋው ጋር ቀበሩት ቀድሞ ስጋው የተቀበረው በታላቁ ነብይ በኤልሳ መቃብር ነበር፤ ቅዱስ ዮሐንስ ሰኔ 30 ልደቱ ነው፤መስከረም 2 አንገቱ የተቆረጠበት ሚያዚያ 15 ያረፈበት፤የካቲት 30 ራሱ የተገለጸበት ነው። ከነዚህ ውስጥ መስከረም 2 እና ሰኔ 30 ቤተክርስቲያን ሰማዕቱን በደማቁ ታዘክረዋለች። ከቅዱስ ዮሐንስ በረከት ያሳትፈን።
(ስንክሳር፤ገድለ ዮሐንስ መጥምቅ የካቲት ወር የሚነበብ)

No comments:

Post a Comment