Tuesday, March 5, 2013

የካቲት 26




"ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፤ እርሱ ሰብሮናልና፥ እርሱም ይፈውሰናል፤ እርሱ መትቶናል፥ እርሱም ይጠግነናል።" ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚያብሔር ሆሴ 61 የካቲት 26 በዚህች ዕለት እውነተኛው ነቢይ ሆሴዕ አረፈ። በትንቢቱ ድንቅ ድንቅ ነገሮችን ተናገረ የእስራኤል ልጆችን ስለ ኃጢያታቸው በግልጽ ዘለፋቸው፤ ስለ ጌታችን ህማም ሞት ተናገረ "ሞት ሆይ ኃይልህ ወዴት አለ ? መቃብርስ ድል መንሳትህ ወዴት አለህ ? " ሆሴ 1314 ስለ እመቤታችን የግብጽ ስደትም ተናግሯል "ልጄን ከግብጽ ጠራሁት" ሆሴ 111 ሌሎች ብዙ ትንቢቶችን እየተናገረ 70 ዓመት ኖሮ በበጎ ሽምግልና በዛሬዋ ዕለት አረፈ። በረከቱ ይደርብን
ምሕረትም የሌላትን እምራለሁ፥ ሕዝቤም ያልሆነውን። አንተ ሕዝቤ ነህ እለዋለሁ፤ እርሱም። አንተ አምላኬ ነህ ይለኛል።
 

No comments:

Post a Comment