Sunday, July 7, 2013

ሰኔ 30






በዚህች ቀን የጌታን መንገድ ጠራጊው፤ሐዋርያው፤ነብዩ ሰማዕቱ ቅዱስ ዮሐንስ የልደት ቀኑ ነው፤ መስከረም 2 አንገቱ የተቆረጠበት ነው ሚያዚያ 15 እረፍቱ ነው፤ አንገቱ ከተቆረጠ በኃላ የተቆረጠች አንገቱ ክንፍ አውጥታ 15 ዓመት በሳውዲአረቢያና አካባቢው ወንጌልን ሰብካለች፤ የካቲት 30 ቀን የዮሐንስ ራስ የተገለጸችበት ቀን ነው። ከነዚህ አራት በዓላት ሁለቱን ቤተክርስቲያን ታቦተህጉን አውጥታ በደማቁ ታከብረዋለች እነዚህም ሰኔ 30 ልደቱና መስከረም ሁለት አንገቱ የተቆረጠበትን ቀን ነው።ጨካኝ ሄሮድስ የቤቴልሔም ህጻናትን ሲጨፈጭፍ መጥምቁ ዮሐንስ ከአናቱ ከቅድስት ኤልሳቤጥ ጋር ወደ ሲና በርሃ ተሰደደ፤ኤልሳቤጥ በጣም አርጅታ ነበር ያን በርሃ ታዲያ እንዴት ቻለችው ያውም ልጅ አዝላ ልጅ ተሸክማ ረዳት ሳይኖራት ብቻዋን፤አባቱ ዘካርያስ በምኩራብ በመሰዊያው ፊት ልጅህን አምጣ ብለው አንገቱን ቆርጠው ገደሉት። ኤልሳቤጥም ሲና በርሃ ላይ ሞተች ህጻኑ ዮሐንስ ብቻውን ቀረ፤ የእናቱን በድነ ስጋ አቅፎ አለቀሰ፤ሁሉን ቻይ ሁሉን የሚያይ፤ ሁሉን የሚመረምር ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ለእመቤታችን እናቴ ሆይ ዘመድሽ ኤልሳቤጥ በበርሃ አርፋለች እንቀብራት ዘንድ እንሂድ አላት ደመና ጠቅሰው ዮሴፍና ሰሎሜን አስከትለው ሄደዋል ገንዘውም ቀብረዋታል፤ ከዚህ በኃላ እመቤታችን ልጄ ወዳጄ ሆይ ዮሐንስን ይዘነው እንሂድ አለችው የለም እናቴ ፤እርሱ እዚው ይቆያል መንገዴን ጠራጊ ነው፤ ኑሮው በዚሁ በርሃ ነው፤ጊዜው ሲደርስ ወደ ዮርዳኖስ ይመጣል ያጠምቀኝማል ያኔ አንድነቴ ሶስትነቴ ይገለጣል አላት፤ ትተውት ተመለሱ ከመሞቱ በፊት እናቱ ያሰፋችለትን የግመል ቆዳ አገልድሞ አንቦጣ የሚባል ቅጠልና የበርሃ ማር እየበላ በበርሃ ኖረ 30 ዓመት 6 ወር ሲሆነው፤የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑእያለ ከበርሃ ወጣ ሉቃ 33 "እውነት እላችኋለሁ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም፤" ማቴ 1111 ይህ የጌታችን ምስክርነት ነው። ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን።


No comments:

Post a Comment