Sunday, July 14, 2013

ሐምሌ 8





በዚህች ቀን ከሮም ነገስታት ወገን የሆነው አባ ኪሮስ አረፈ፡፡ አባ ኪሮስ አባቱ ንጉስ ዮናስ እናቱ አንስራ ይባላሉ፡፡ ሀገሩ ሮም ነው፡፡ ወላጆቹ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ቅዱሳን ነበሩና አቡነ ኪሮስ በታህሳስ 8 ወለዱ፡፡ አቡነ ኪሮስ የመጀመሪያ ስሙ ዲላሶር ይባል ነበር፡፡ በኋላ አባቱ ከሞተ በኋላ ሀብቱን ከወንድሙ ተካፍሎ ለድሆች መጽውቶ ዓለምን ንቆ መንኖ ሄደ፡፡ ከአባ በቡነዳ ገዳም ገባ፡፡ በ17 ዓመቱ ሥርዓተ ምነኩስናን ተማረ፡፡ በአባ በቡነዳ እጅ መነኮሰ፡፡ ከዚህ በኋላ በጾም በጸሎት ተወስኖ ኖረ፡፡ስለ ዓለም መከራ ለ40 ዘመን ተኝተው ሲጸልዩ እላያቸው ላይ ሳር በቅሎባቸው ሳለ መላእክት መጥተው ተነስ ቢሉት አዳም የፍጡር ቃል ሰምቶ ወድቀዋል ጌታዬ ድምጹን ያሰማኝ አላቸው በኋላ ኪሩቤል አንስቶ ወስዶ ገነት አሳይተውት ጌታችንም ቃል ኪዳን ሰቷቸዋል፡፡
ቃል ኪዳናቸውም ፡- መካኖች ልጀ የሌላቸው ገድሉን አቅፈው ቢያለቅሱ ጸበሉን ቢጠጡ ስምህን ቢጠሩ፤ የመካኒቱን ማህጸን እከፍታለሁ፡፡ የሚሞትባቸውን እንዳይሞተባቸው አደርጋለሁ፡ በንጹ ገንዘቡ ቂምና በቀል ሳይዝ በህግ በስጋውና በደሙ የጸና ሰው በስምህም በተሠራው ቤተክርስቲያን ጧፍ ዘይት ያበራ መገበሪያ ያመጣውን ልጅ አሰጠዋለሁ፡፡ ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ከዚም በኋላ በተወለዱ 270 ዓመቱ ሐምሌ 8 አርፏል፡፡
አባታችን አቡነ ኪሮስ በመዲናችን አዲስ አበባ በኮተቤ መስመር በስማቸው ታላቅ ቤተክርስቲያን አላቸው ሐምሌ 8 ታቦታቸው ወጥቶ በደማቁ ተከብሮ ይውላል፡፡ ልጅ የሌላቸው እናትና እህቶቻችን ገድላቸውን አዝለው ልጅ እንዲሰጧቸው ስለት ይሳላሉ በዓመቱም ልጅ አዝለው መጥተው ስለታቸውን ይከፍላሉ፡፡ ይህንንም በአይናችን አይተን በጆሯችን ሰምተን ይኸው እንመሰክራለን ፡፡ ከቅዱሳን ሁሉ ረድኤታቸውንና በረከታቸውን ይደርብን፡፡

LIKE >>>
https://www.facebook.com/pages/ተዋህዶ-ሀይማኖታችን/117298008428339?ref=hl

3 comments:

  1. This comment has been removed by the author.

    ReplyDelete
  2. le Amelkae kibr misgana yihun.Elelelelelelelee Min yisanewale? minim minim! Sile hulu enamesegenewale.

    ReplyDelete
  3. አባታችንን፡አባ፡ኪሮስን፡የሰጠን፡አምላከ፡አባ፡ኪሮስ፣መድሐኒአለም፡ክርስቶስ፡ምስጋና፡ይድረሰው፡፡እኔና፡ባለቤቴ፡ለእኚህ፡ፃድቅና፡ለተቀደሰው፡ቅዱስ፡ቦታ፡ምስክሮች፡ነን፡፡እንደ፡አምላክ፡ፈቃድ፡ጋብቻችንን፡በስርዐተ፡ቤ\ክ፡ነበር፡የተፈፀመው፡፡ ለ4፡አመት፡ያለልጅ፡ነበር፡የኖርነው፡፡የመጨረሻውን፡ሁለት፡አመት፡ደጅ፡ስንጠና፡ቆዬን፡የአምላክ፡ፈቃድ፡ሆኖ፡በdv፡ወደ፡usa፡ልንመጣ፡ስንዘጋጅ፡ምንም፡የማይሳነው፡አምላከ፡አባ፡ኪሮስ፡የአይናችን፡ማረፊያ፡የሚሆን፡ወንድ፡ልጅ፡ሰጠን፡ሀሳባችንንም፡ሞላልን፡፡ዛሬ፡በአባታችን፡ስም፡የሚጠሩ፡የ3፡ልጆች፡አባት፡ሆኛለው፡፡መካኒቱ ሰባት ወልዳለችና፥ልጅ፡በማጣት፡ያዘናችሁ፡አምላከ፡አባኪሮስ፡የልባችሁን፡ሀዘን፡ያርቀላችሁዋል፡፡ መዝሙረ ዳዊት127፥3 እነሆ፥ ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው፥ የሆድም ፍሬ የእርሱ ዋጋ ነው።
    ስብሀት፡ወአኮቴት፡ለአምላከ፡ቅዱሳን።ወለወላዲቱ፡ድንግል

    ReplyDelete