Thursday, July 25, 2013

ሐምሌ 18



 በዚህች ቀን በመጽሐፍ ቅዱስ የጌታ ወንድም ተብሎ የተገለጸው የጻድቁ የዮሴፍ ልጅ ሐዋርያው ያዕቆብ በሰማዕትነት አረፈ፤ ሐዋርያት ወንጌል ለማስተማር ዓለምን በእጣ ሲከፋፈሉ፤ ቅዱስ ያዕቆብ እጅግ አብዝቶ ቆሞ ከመጸለዩና ስግደት ከማብዛቱ የተነሳ እግሩ በጣም አብጦ ስለነበር ተዘዋውሮ ማስተማር አይሆንለትም ብለው እዚያው እየሩሳሌም እንዲያስተምር አደረጉት፤ብዙ አይሁዳውያንን ክርስቶስን ወደ ማመን መለሰ፤በመጨረሻም በዛሬዋ ዕለት በአይሁድ አማጽያን እጅ በሰማዕትነት አረፈ፤በረከቱ ይደርብን

No comments:

Post a Comment