Saturday, July 20, 2013

ሐምሌ 14


በዚህች ቀን ቅዱስ አብሮኮሮንዮስ በሰማዕትነት አረፈ።ትውልዱ እየሩሳሌም ነው፤ እናቱ ጣኦት አምላኪ ነበረች እርሱም ጣኦት እንዲያመልክ ለጣኦት እንዲሰግድ ግድ አለችው እርሱም ክርስቶስን ነው የማመልከው አይሆንም ባላት ጊዜ ለንጉሱ ተናገረች የገዛ ልጇን አሳልፋ ሰጠች፤ ብዙ መከራ ተቀበለ በዛሬዋም ቀን በሰይፍ አንገቱን ቆርጠው ገደሉት፤የሰማእትነት አክሊል ተቀበለ። ግን አናት ልጇን ለሞት አሳልፋ እንደሰጠች ያየ የሰማ ማን ነው ? " እናትና አባቴ ተዉኝ እግዚያብሔር ግን ተቀበለኝ" ያለው ዳዊት ለካስ እውነቱን ነው፤ የዚህ አባት በረከት ይደርብን

LIKE >>>
https://www.facebook.com/pages/ተዋህዶ-ሀይማኖታችን/117298008428339?ref=hl

No comments:

Post a Comment