Tuesday, February 25, 2014

የካቲት 13በዚህች ቀን መልካም ስም አጠራር ጣፋጭ ዜና ያለው 2ኛው አውሳብዮስ የእረፍት ቀኑ ነው፤ ይህ አባት ሌሊት ሌሊት ከሚስቱ ጋር ባህር ውስጥ ቆመው ሲጸልዩ ያድራሉ አራት ስግደት በየቀኑ ይሰገዳሉ አብዝተው ይጾሙ ይጸልዩም ነበር። የንጉሱ ሚስት በዝሙት በፈተነችው ጊዜ አይሆንም አላት ዘፍ 39 12 ለንጉሱ አስገድዶ ሊደፍረኝ ነበር ስትል ነገረችው እርሱ ተናዶ ጽኑ ስቃይ አጸናበት ቅዱስ ኡራኤል ነጥቆ ወደ ሰማይ አወጣው በዚያም 14 ዓመት ኖረ 2 ቆሮ 122 ዳግመኛ ወደ ምድር ተመልሶ 40 ዓመት ወንጌልን ሰበከ ሰማኒያ አምስት አረማውያንን ወደ ቀናች ሃይማኖት መልሷል። ይህ አባት በቅድስና ኖሮ በዛሬዋ ዕለት አርፏል በረከቱ ይደርብን።

No comments:

Post a Comment