Wednesday, November 28, 2012

አሥሩ ትእዛዛት



 
እግዚአብሔር አምላካችን እጅግ በጣም የሚወደን እና የሚያስብልን አባታችን ነው፡፡ እርሱ ደግሞ ሁሉንም የሚያውቅ ስለሆነ ለእኛ ምን እንደሚጠቅመን፤ምን እንደሚያስፈልገን፤ምን እንደሚጎዳን ሰለሚያውቅ አሥሩን ትእዛዛት ሰጠን፡፡

 እነዚህም፡-
          1.ከኔ በቀር ሌሎችን አማልክት አታምልክ
          2.የእግዚአብሔር አምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ
          3.የሰንበትን ቀን አክብር
          4.አባትና እናትህን አክብር
          5.አትግደል
          6.አታመንዝር
          7.አትስረቅ
          8.በሐሰት አትመስክር
          9.የባልንጀራህን ቤት አትመኝ
         10.ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ የሚሉት ናቸው፡፡

እነዚህ ትዕዛዞች ሁሉም ሰው እንዲያደርጋቸው ርህሩህ አባታችን እግዚአብሔር አዞናል፡፡ እነዚህ ትዕዛዞችን ከፈጸምን እግዚአብሔር ይወደናል፤በረከትም ይሰጠናል፡፡

እግዚአብሄርን እንወደዋለን አይደል? እግዚአብሄርን መውደዳችን የሚታወቀው ደግሞ አድርጉ ያለንን ስናደርግ፤ አታድርጉ ያለንን ደግሞ የማናደርግ ከሆነ ነው፡፡ይህን ካደረግንእግዚአብሔር በእኛ ደስ ይለዋል፤ ይባርከናል፤የሚያስፈልገንን ሁሉ ይሰጠናል፡፡ እነዚህ ትዕዛዛት ካልፈጸምን  ግን እግዚአብሔር ያዝንብናል፤ ከደጉ አምላካችንም እንለያያለን፡፡ ከአምላካችን ከተለየን ደግሞ ጥሩ ነገር አይኖረንም፡፡ ስለዚህ  እነዚህን ትእዛዛት ልንፈጽማቸው ይገባል፡፡

እመቤት ፈለገ

No comments:

Post a Comment