Tuesday, November 6, 2012

ሰላም ተዋሕዶ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን


ሰላም ተዋሕዶ ሰላም ኦርቶዶክስ

የአትናትዮስ ሐውልት የዲዮስቆሮስ

የአዳም መመኪያ የሔዋን ሀገር



አንቺ አይደለሽም ወይ የቅዱሳን ክብር

የአብርሃም ቃልኪዳን የአቤል መስዋዕት

የሔኖክ ሃይማኖት ያዳንሽው ከሞት

አንቺ የኖህ መርከብ ዕፀ መድኃኒት፡፡

በአብርሃም ድንኳን ተወልደሽ ያደግሽ


የይስሐቅ መአዛ ወደር የሌለሽ

የዮሴፍም አፅናኝ ተዋሕዶ ነሽ፡፡

የሙሴ ጽላት ነሽ የአሮን በትር

የኢያሱ ሐውልት የጌዲዮን ፀምር

የሳሙኤል ሙዳይ የእሴይ ትውልድ

የዳዊት በገና የሰሎሞን ዘውድ

የታተመች ገነት የምስጢር ጉድጓድ፡፡

ቱሳሔና ሚጠት ውላጤም ጭምር

ያልተቀላቀለሽ ንጽሕቲቱ ምድር

ኢሳይያስም አይቶ በሩቅ መነፅር

ስለ ቅድስና ሆነ ያነቺ ምስክር፡፡

የነ ኤልያስ ቤት የወርቅ መሶብ

ውስጥሽ የተሞላ የምስጢር ምግብ

የኤልሳ ማሰሮ የሕይወት መዝገብ፡፡

ፋራን የምትባይ የእንባቆም ተራራ

ሁሉንም የምታሳይ በቀኝም በግራ፡፡

የሕዝቅኤል አልፍኝ ባለ አንድ በራፍ

የማትከፈችው የኬልቄዶን ቁልፍ፡፡

የሕግ መፍለቂያ የነፃነት ቦታ

የሚክያስ ሀገር አንቺ ነሽ አፍራታ፡፡

በውስጥም በውጭም የሌለብሽ እንከን

የሕይወት መዝገብ ነሽ ተዋሕዶአችን፡፡

ሐዋርያት ይምጡ ያውሩ ያንቺን ዜና

የሚያውቅ ሲናገር ደስ ያሰኛልና፡፡

ሰማዕታት ልጆችሽ የፃፉልሽ በደም

የሕይወት መጽሐፍ ነሽ የጽድቅ የሰላም

No comments:

Post a Comment