Wednesday, November 7, 2012

መስከረም 2



በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
 
መስከረም 2



በዚህች ቀን መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ አንገቱ የተቆረጠበት ቀን ነው። የ 2 ዓመት ከመንፈቅ ህጻን እያለ ከእናቱ ኤልሳቤጥ ጋር ወደ ሲና በርሃ ተሰደደ፤ በ 7 ዓመቱ እናቱ በርሃ ላይ ሞተችበት በድኗን ታቅፎ አለቀሰ፤ በዚህ ወቅት ጌታችን ህጻን ነበር ለእመቤታችን ዘመድሽ ኤልሳቤጥ አርፋለችና ወደዚያው እንሂድ አላት ዮሴፍና ሶሎሜን ጨምረው ወደ ዮሐንስ መጡ ብቻውንም ሲያለቅስ አገኙት፤ ኤልሳቤጥን ገንዘው ቀበሯት፤ እመቤታችን ለጌታ ዮሐንስን ይዘነው እንሂድ አለችው፤ ጌታም የለም መንገዴን ጠራጊ ነውና እዚሁ በረሃ ነው የሚያድገው አላት። ቅዱስ ዮሐንስ ኤልሳቤጥ ያሰፋችለት የግመል ቆዳ ነበረች እርሷን ለብሶ አንቦጣ የሚባል ቅጠልና የበርሃ ማር እየበላ በብህትውና ኖረ።30 ዓመት ከመንፈቅ ሲሆነው ወደ ዮርዳኖስ ወጣ የጌታን መንገድ አቅኑ እያለ አዋጅ ተናገረ ጌታንም አጠመቀ፤ ጳጉሜ 1 ሄሮድስ እስርቤት ከተተው በዛሬዋ ቀንም አንገቱን ቆረጠው፤ የተቆረጠች አንገቱ ክንፍ አውጥታ 15 ዓመት በደቡብ አረቢያና አካባቢው ሰብካ ሚያዚያ 15 ቀን በክብር አረፈ፤ ደቀመዛሙርቱ ከቀሪው አካሉ ጋር አድርገው ቀበሩት። በረከቱ ይደርብን




ይህን ቢቡት

 

No comments:

Post a Comment