Showing posts with label ልዩ ልዩ. Show all posts
Showing posts with label ልዩ ልዩ. Show all posts
Monday, October 2, 2023
Wednesday, February 23, 2022
💚 💛❤️ ማንኛውንም ሥዕላት/ቅዱሳን ሥዕላት ለገዳማት፡ ለቤተክርስትያናት ለወዳጅ ለዘመድ ማሠራት ከፈለጉ 💚 💛❤️
ማንኛውንም የሥዕል ዓይነት ለማሠራት ስትፈልጉ ከሥር ያለውን አድራሻ መጠቀም ትችላላችሁ።







Wednesday, January 12, 2022
ይህን ያውቁ ኖሯል?
የመነኮሳት ሕይወት
ምንም እንኳን የድንግልናና የምናኔ ኑሮ ቀደም ብሎ የተጀመረ ቢሆንም የምንኩስና መሥራችና አባት ቅዱስ እንጦንስ ነው፡፡ አባ እንጦንስ ግብፅ ውስጥ በምትገኝ ቆማ በምትባል ቦታ በ251 ዓ.ም ተወለደ፡፡ ወላጆቹ ሀብታሞችና ደጋግ ሰዎች ነበሩ፡፡ ከወላጆቹ ዕረፍት በኋላ የነበረውን ሀብት ለድሆች መጽውቶ መንኩሶ ብዙ ዓመት በብሕትውና ኖረ፡፡
በዚያን ጊዜ ብዙ ታምራትን ስለሠራ ሕዝቡ ግማሹ እሱን አይቶ ለማድነቅ የቀረው ደግሞ በእርሱ ጸሎት ለመፈወስ ወደነበረበት ቦታ ይጐርፍ ነበር፡፡ እርሱም በ356 ዓ.ም ዐረፈ፡፡
አባ ጳኩሚስ የተባለ ሌላው አባት በላይኛው ግብፅ ውስጥ ብዙ ገዳማትን በመሥራት የምንኩስናን ሕግና ሥርዓት በመወሰን ስለምንኩስና መስፋፋት ብዙ ደክሟል /290-347 ዓ.ም/፡፡ አንድ ቀን ወደ ዱር እንጨት ፍለጋ ሔዶ ሳለ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጸለትና እንደ አባቶቻችን ሐዋርያት የአንድነትን ማኅበር ለመሥራት መነኮሳትን እንዲሰበስብ አዘዘው፡፡ ብዙ አማኞች እየናፈቁት ማግኘት ያልቻሉትን ገዳማዊ ሕይወት ያገኙ ዘንድ ገዳም ለመመሥረት የሚስችለውንና የሚያስተዳድርበትን በነሐስ ላይ የተቀረጸ ሕግ ሰጠው፡፡ አባ ጳኩሚስም ከመልአኩ በተሰጠው ሕግ መሠረት የሚተዳደር ገዳም አቋቋመ፡፡ ይኸውም መነኮሳቱ ጠዋትና ማታ አብረው እንዲፀልዩ በአንድነት እንዲሠሩ ገቢና ወጪያቸው አንድ ላይ እንዲሆን በአንድነት እንዲመገቡ፣ ልብሳቸው አንድ አይነት እንዲሆንና እነዚህን የመሳሰሉትን ደንቦች አወጣላቸው፡፡ በዚህ መሠረት መነኮሳቱ የዕለት ምግባቸውን የሚያገኙት እየሠሩ ነበር፡፡ ከሴቶችም የምንኩስናን ሕይወት የጀመረች የአባ ጳኩሚስ እህት ማርያም ናት፡፡
ከዚህ በኋላ በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ጀምሮ ምንኩስና በግሪክ፣ በሮም፣ በሶሪያና በሌሎችም ሀገሮችም እየተስፋፋ ሄደ፡፡
የምንኩስናን ሕይወት ወደ ኢትዮጵያ ያመጡ በ5ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በጉባዔ ኬልቄዶን /በሃይማኖት ስደት/ ምክንያት ከቁስጥንጥንያ፣ ከግብፅ፣ ከሶርያ፣ ከሮም፣ ከአንጾኪያ ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ዘጠኙ ቅዱሳን መነኮሳት ናቸው፡፡ ምንኩስና ከተመሠረተ ጀምሮ በየጊዜው ሕዝቡ ታላላቆችም ሳይቀሩ ወደ ገዳማቱ እየሄዱ ይመነኩሱ ነበር፡፡
ነገር ግን ከ9ኛው መቶ ዘመን ጀምሮ በማኅበር ከሚኖሩት መነኮሳት መካከል ጥቂቶቹ ቀስ በቀስ ለብቻ በተለየ ቤት መኖር እያንዳንዱ መነኩሴ ለብቻ በፈለገበት ጊዜ መብላትና መተኛት ስለጀመረ በየገዳማቱ የመነኮሳቱ ኑሮ በማኅበር የሚኖሩትና ለብቻቸው የሚኖሩት ለሁለት ተከፈሉ፡፡
የድንግልና መሠረቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «ስለ መንግሥተ ሰማያት ሰውነታቸውን ጃንደረባ ያደረጉ አሉና፤ መፈጸም የሚችል ግን ይፈጽም» ሲል የተናገረው የሕግ ቃል ነው፡፡ ማቴ. 19፡12
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
/ምንጭ፦ ‘የዛሬዋ ኢትዮጵያ በመጽሐፍ ቅዱስ’ በዲ/ን አሐዱ አስረስ፣ ነሐሴ 1992 ዓ.ም/
Monday, January 10, 2022
የእመቤታችን ሥዕል ከመንበር ላይ ለምን ይቀመጣል?
ይህን ያውቁ ኖሯል?
የእመቤታችን ሥዕል ከመንበር ላይ ለምን ይቀመጣል?
በኦሪቱ የኪሩቤል ሥዕል በታቦቱ አጠገብ ይቀመጥ ነበር፡፡ ዘጸ. ፳፭፥፳፩-፳፪፤ዘኊ ፯፥፹፱፡፡ እግዚአብሔር ለሙሴ ነግሮ እንዲህ እንዲሆን ያደረገበት ምክንያት አለው፡፡ይህም ምክንያት ኪሩቤል የመንበሩ /የዙፋኑ/ ተሸካሚዎች በመሆናቸው ነው፡፡ ፩ኛ ሳሙ.፬፥፬፤ ሕዝ.፩፥፭፰፤ ፲፥፲፪፤ ፳፩፤ራእ.፬፥፮፡፡ በአዲስ ኪዳን ደግሞ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአዲስ ኪዳን ኪሩብ ትባላለች፡፡ እንዲያውም ከኪሩቤል ትበልጣለች፡፡ ኪሩቤል የሚሸከሙት መንበሩን ነው፤ እመቤታችን ግን ማኅፀኗን መንበር አድርጋ እርሱን ተሸከመችው፡፡ እንግዲህ በብሉይ ኪዳን ዘመን በእግዚአብሔር ትእዛዝ የኪሩቤል ሥዕል በመንበረ ታቦቱ ይቀመጥ እንደ ነበር በአዲስ ኪዳን ደግሞ ኪሩብ የምትባል እመቤታችን ሥዕሏ በመንበረ ታቦቱ ላይ ይቀመጣል፡፡
ምንጭ፡ ነገረ ቅዱሳን ቁ. ፩
Tuesday, December 25, 2012
ላፍቶ ሌንቃ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ሁኔታ
ቦታው ከአ.አ 210 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ከምትገኘዋ ላፍቶ ሌንቃ የምትባል የገጠር ከተማ ሲደርሱ ወደ ቀኝ የሚገነጠለውን እና ወደ ስልጤ ዞን እና ቄልጦ ከተማ የሚወስደውን ኮረኮንቻማ የገጠር መንገድ ይዘው ሲጓዙ በግምት ከ4-5 ኪ.ሜ በኋላ ያገኙታል፡፡ ታሪክ ቤተክርስቲያኑ የተመሰረተበትን ዘመን በእርግጠኝነት ለማወቅ እና እና ለመናገር የሚያስችል በቂ መረጃ የሌለ ቢሆንም በጣም ብዙ የሆኑ ዘመናትን እንዳስቆጠረ የሀገር ሽማግሌዎች የተናገሩ እና በአካባቢው ላይ ያሉ የጥንት አባቶች ሲጠቀሙበት የነበሩ ዋሻዎች በውስጣቸውም የተገኘው የመስቀል ምልክት እና ፅሁፍ ምስክር ሲሆኑ በይበልጥ ግን ጥናት እና ምርምር ሊደረግበት የሚገባው ነገር ነው፡፡ ተጨባጭ ሁኔታ
ይህ ቤተክርስቲያን አሁን ያለበት ሁኔታ እስከ ዛሬ ካየነው ከሠማነው ሁሉ የሚለይ እና እጅግ የሚያሳዝን ሁኔታ ነው፡፡ ሌሎች ቦታዎች ቢያንስ የሚያፈሱ ያረጁ በመቃብር ቤት ያሉ…. ብቻ የሆነ ትንሽ ነገር ያላቸው ናቸው፡፡ እዚህ ግን ምንም የለም እንደ ቤተክርስቲያን የሚያገለግለው ዋርካ/ዛፍ/ ሲሆን ከስሩ ስዕለ መድኃኔዓለምን በማስቀመጥ ይጠቀሙበታል፡፡ በፊት የነበረው ቤተክርስቲያን በተለያየ ጊዜ የተነሱ አፅራረ ቤተክርስቲያን ለ 3 ጊዜ ያፈረሱት ሲሆን ለመጨረሻ ጊዜ በ1971 ዓ.ም ከዛሬ 32 ዓመታት በፊት በአህዛብ የተቃጠለ ሲሆን እስከ አሁን ድረስ ለዚህን ያህል ዓመታት ሙሉ በአካባቢው ያሉት 7ዐ ክርስቲያኖች ቤተክርስቲያን አግኝተው/አይተው/አያውቁም ነገር ግን ሃይማኖታችንን አንክድም ማተባችንን አንበጥስም በማለት ያለ መምህር በመፅናት ለብዙዎች አርአያ ለመሆን የሚችሉ ዕንቊ የቤተክርስቲያን ልጆች ያሉበት ቦታ ነው፡፡ እነዚህ ምእመናን ለ 32 ዓመታት ያሳለፉትን ጭንቅ /መከራ/ ተናግሮ መጨረስ የማይቻል በሰው አእምሮ የማይገመት አሰቃቂ ለመግለፅም የሚከብድ ነው፡፡ የቤተክርስቲያኑን ይዞታ አንሰጥም በማለታቸው ምክንያት ከ4 ጊዜ በላይ ታስረዋል ተገርፈዋል መከራም ደርሶባቸዋል፡፡ ልጅ ወልደው ክርስትና ማስነሳት ንስሀ መግባት ማስቀደስ…. የማይታሰቡ ነገሮች ናቸው፡፡ ሰው ሲሞት እንኳ ጸሎተ ፍትሀት ሳይደረግለት ዝም ብለው ቤተክርስቲያኑ የተቃጠለበት ቦታ አምጥተው ይቀብሩታል፡፡ አስከ አሁንም ድረስ የልጅነት ጥምቀት ያልተጠመቁ ህፃናት እና ወጣቶች ያሉ ሲሆን አንገታቸው ላይ ማህተብ በማሰር እኔ ክርስቲያን ነኝ በማለት በአህዛብ መካከል ይመሰክራሉ፡፡ ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ በእለተ ሰንበት ተኝቶ አያረፍድም ወንዱም ሴቱም ህፃናቱም ትልልቆቹም ነጠላቸውን አጣፍተው ጋቢያቸውን አደግድገው ቤተክርስቲያኑ የተቃጠለበት ቦታ የምትገኝ አንድ ዛፍ ስር የመድኃኔዓለምን ስዕል በማኖር/በማስቀመጥ/ ይሰግዳሉ ይማፀናሉ፣ይለምናሉ ሥርዓተ አምልኮታቸውንም ይፈፅማሉ፡፡ ወር በገባ በ27 የመድኃኔዓለም ዕለት ተራ ይዘው ዳቦ በመጋገር ጠላ በመጥመቅ / ጠበል ፀዲቅ በማዘጋጀት/ መድኃኔዓለምን ይዘክራሉ፡፡ በአጠቃላይ በአህዛብ ተከበው ሃይማኖትን በማፅናት አስደናቂ ተጋድሎ በመፈፀም ላይ ይገኛሉ፡፡
ተአምራት፡- በቦታው ላይ የተገለጡት ብዙ ተአምራት ቢሆኑም ለጊዜው ጥቂቶቹ
1. ቤተክርስቲያኑን ያቃጠሉት 2 ወንድ እና 1 ሴት አህዛብ ሲሆኑ፡- ሴቲቱ እሳት በእንስራ ደብቃ ይዛ በመምጣት ቤተክርስቲያኑ በር ላይ ይጠብgት ለነበሩ 2ቱ ወንዶች በመስጠት ተባብረው ካቃጠሉት በኋላ በተለያየ ወር የመድኃኔዓለም እለት 2ቱም ወንዶች በመብረቅ የተቀጡ /የሞቱ/ መሆናቸው፡፡ሴቲቱም ከብቶችዋ በሙሉ በመብረቅ ማለቃቸው፤
2. ቤተክርስቲያኑ ሲቃጠል የነበሩ አገልጋይ መልሶ ለማሰራት የተሰበሰበውን ብዙ ገንዘብ በእጃቸው አድርገው ከአገልጋያቸው ጭምር ወደ እስልምና በገቡ በእለቱ አይነስውር መሆናቸው አገልጋዩም ሽባ መሆኑ እና እስከዛሬ በህይወት መኖራቸው፤
3. ቤተክርስቲያኑ በተቃጠለበት ቦታ እና አፀዶች መካከል ዝማሬ ቃጭልና እና ከበሮ የሚሰማ ዕጣን /ማዕጠንት/ የሚሸት መሆኑ
4. ጥንታውያን ዋሻዎች /ሰው የሚገባባቸው እና የማይገባባቸው/ሲኖሩ በድፍረት የገቡት አንደበተ-ዲዳ፤ዓይነ-ስውር መሆን እና በእሳት እየተቃጠሉ መውጣት በተጨማሪም ዝማሬ ቅዳሴ ወዘተ በዋሻዎቹ ውስጥ መሰማት ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ በተጨማሪም በተለያዩ ቅዱሳት/ቅዱሳን/ ስም የተሰየሙ ፍል/ሙቅ/ጠበሎች ያሉ ሲሆን ህዝብም አህዛብም እየተጠቀሙባቸው በመፈወስ ላይ ይገኛሉ፡፡ ቀጣይ ተግባር፡- በሀዲያ እና ስልጢ ሀገረ ስብከት ውስጥ ያሉትን ችግሮች እና በምእመናኑም ላይ የሚደርሰውን መከራ እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ለማስወገድ በማሰብ የቤተክርስቲያን ልጆች በመሰባሰብ እና በመምከር ከሀገረ ስብከቱ ጋር በመነጋገር አብሮ በመስራት እና እውቅና በመውሰድ በመጀመሪያ ደረጃ የላፍቶ ሌንቃ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያንን በተገቢው ሁኔታ እና በአጭር ጊዜ ለማቋቋም፤ በቀጣይነት ደግሞ ሀገረ ስብከቱን ማዕከል ባደረገ ሁኔታ ያሉትን ችግሮች ለዘለቄታው ለመቅረፍ እና ለማስወገድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሀዲያ እና ስልጤ ሀገረ ስብከት ቅዱስ
እንጦንስ መንፈሳዊ
የአገልግሎት ማኅበር” ማኅበር ተቋቁሞ የተለያዩ ተግባራት በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ማንኛውም የቤተክርስቲያን ነገር የሚያሳስበው አካል ማኅበራትም ሆኑ ምእመናን ከዚህ የባሰ ሁኔታ ስለሌለ በኅብረት ሆነን አስቸኳይ እና ዘለቄታዊ መፍትሄ እንድንሰጥ ሁላችንም የምንችለውን ሁሉ እና የሚጠበቅብንን እንድናደርግ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ 50 ሎሚ ለ1 ሰው ሸክሙ ነው ለ50
ሰዎች ግን ጌጥ ነው እንርዳዳ ይህችን ቤተክርስትያን እንጨርስ ከእግዚያአብሔር ጋራ
ህንፃ ቤተክርስቲያኑ እየተሰራ ሲሆን
የቤተ ክርስቲያኑን ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ በተቸላችሁ መርዳት ይቻላል..ኑ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ እንስራ መ.ነህ 2:20… ቅዱስ እንጦንስ መንፈሳዊ የአገልግሎት ማኅበር
Commercial Bank of Ethiopia, Bomb Tera Branch. Account no. 1000017080249 mobile
+251911143653, +251911780816, +251910016008 ክብር
ምስጋና ለመድሓኔአለም
ይሁን፡፡ለፍፃሜው አድርሶ
የበረከቱ ተካፋይ
ለመሆን ያብቃን፡፡በርቱ
እመቤቴ ከነልጅዋ
ትርዳችሁ ትርዳን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!
Subscribe to:
Posts (Atom)
