Monday, November 26, 2012

ህዳር 18



በዚህች ቀን ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የሆነው ሐዋርያው ፊሊጶስ አረፈ፤ ጥቅምት 14 ቀን መታሰቢያውን የምናከብርለት ኢትዮጰያዊውን ጀንደረባ ያጠመቀውን ዲያቆኑ ፊሊጶስ ነው ይህ የዛሬው ግን ቁጥሩ 12 ሐዋርያት ነው ዮሐ 144 በነገው ኢየሱስ ወደ ገሊላ ሊወጣ ወደደ፥ ፊልጶስንም አገኘና። ተከተለኝ አለው።ፊልጶስም ከእንድርያስና ከጴጥሮስ ከተማ ከቤተ ሳይዳ ነበረ ይላል። ሐዋርያት ዓለምን ዞረው ለማስተማር ዕጣ ሲያወጡ ለፊሊጶስ ከወርቅ የተሰራ ኦሞራ የሚያመልኩ ሰዎች ያሉበት አገር ደረሰው ገድለ ሐዋርያት ላይ አፍራቅያ ይለዋል የአገሩን ስም ቱርክ አካባቢ የሚገኝ ነው፤ ወደ ከተማው ግብቶ ወንጌለ መንግስተ ሰማያትን ሰበከ ብዙዎችንም አሳመነ አጠመቃቸው፤ አቆረባቸውም፤ ቤተክርስቲያን ሰራላቸው፤ ካህንና ዲያቆንም ሾመላቸው፤ ነገር ግን ጥቅማቸው የጎደለባቸው የጣኦት ካህናት ከንጉሱ ጋር ነገር ሰርተው አጣሉት፤ አስረው ደበደቡት፤ ሰቅለውም ገደሉት ይህም የሆነው በዛሬዋ ቀን፤ የሐዋርያው በረከት ይደርብን፤
 ሐዋርያ ሰማዕት አንተ የወንጌል ሰው
ትምህርተ ወንጌልን ለዓለም ያበራኸው
ወልድ ዋህድ ብለህ ዞረህ ስትመሰክር
መከራን ተቀበልክ ስለ ጌታ ፍቅር

 
+++++ ከሐዋርያውና ከሰማዕቱ ከቅዱስ ፊሊጶስ በረከት ረድኤት ይክፈለን++++

No comments:

Post a Comment