Thursday, April 4, 2013

መጋቢት 27






የጌታችን ጥንተ ስቅለቱ ነው። ዳግመኛ በዛሬዋ ቀን በኢትዮጵያ ምድር ታላቅ አባት በሰማእትነት አርፏል ይህም ዓፄ ገላውዴዎስ ነው፤ ይህ አባት ቤተክርስቲያን የቅድስና ማእረግ ሰጥታ ከምታዘክራቸው ነገስታት የመጨረሻው ንጉስ ነው። ከዚህ በኃላ በኢትዮጵያ ምድር የነገሱት ነገስታት ምን ደግ ስራ ቢሰሩ የቅድስና ማዕረገ አላገኙም። ዓፄ ገላውዴዎስ የዓፄ... ልብነ ድንግል ልጅ ናቸው፤ ግራኝ መሐመድ ኢትዮጵያን ሲወር ከአባታቸው ጋር ሸሽተው ወደ ደብረ ዳሞ ሄዱ በዚያም 17 ዓመት ቆዩ አባታቸው ዓፄ ልብነ ድንግል ሲሞቱ ወራሽ ሆነው ነገሱ ጦራቸውን አደራጁ ከፖርጁጋሎች ጋር ሆነው ግራኝን ገጠሙት ለየካቲት ማርያም 1543 / ወይናደጋ በተባለ ቦታ ላይ ድል አደረጉት ግራኝ ሞተ የቀሩት ሸሹ ይላል፡፡ በጦርነቱ ማግስት ፖርቹጋሎችአባትህ ቃል በገባልን መሰረት አገር ቆርሰህ ስጠን ሃይማኖታችሁንም ለውጣችሁ የካቶሊክን እምነት ተቀበሉአሏቸው፤ዓፄ ገላውዴዎስም ሲመልሱአገር ቆርሰን አንሰጥም ሃይማኖትም አንለውጥም፤ ለዋላችሁልን ውለታ ግን ወርቅ ብር እንሰጣቹሃለን አሏቸው !!! ብልህ መሪ ይሉሃል ይህ ነው፤ኢይኀድጋ እግዚብሔር ለብሔር ዘእንበለ አሐዱ ሄር” “ እግዚያብሔር አገርን ያለ አንድ ጠባቂ አይተዋትም ማለት ነው። በዓፄ ገላውዴዎስ መልስ የፖርቹጋሉ ጦር አዛዠ ቤርሙዳ ተቆጣ በስውርም ሊያስገድሏቸው አስቦ አልተሳካለትም። ከዚህ በኃላ ግራኝ ያጠፋውን አገር ማቅናት፤ የተጎዳ የተሰደደውን ህዝብ ማጽናናት ጀመሩ ከአቡነ ዮሳብ ጋር ሆነው ስርዓተ ቤተክርስቲያንን አጸኑ ብዙ አብያተክርስቲያናትን አነጹ። ከዚህ በኃላ እንዲህ ሆነ የሐረሩን ገዢ ኑር መሐመድን ጦሩን አደራጀቱ መጣ ዘመኑ 1552 / ወርሃ መጋቢት በሃያ ሰባተኛው ቀን ዕለቱ ደግሞ ዓርብ ነው ከሶስት ቀን በኃላ ፋሲካ ነው፤ በዙሪያቸው ያሉት መኳንንት መሳፍንቱ አማካሪዎቻቸው ፋሲካን አክብረን ጦርነቱን ብንጀምር ይሻላል አሏቸው፤ ዓፄ ገላውዲዎስ ሲመልሱ እንዲህ አሉ እኔስ ፋሲካን ከጌታዬ ጋር በሰማይ አከብራለሁ ጦርነቱ መጀመር አለበት አሉ ትንቢታዊ ንግግር ነበር፤ ጦርነቱ ተጀመረ ከፊት ሆነውም ሲዋጉ ሲያዋጉ ውለው ማምሻውን በጥይት ተመትተው ወደቁ አንገታቸውንም ቆርጠው ገደሏቸው። ታዲያ ህዝቡ እንዲህ ብሎ አለቀሰላቸው፤
ዓፄ ገላውዴዎስ ጌታን ተከተለ
ፋሲካውን ሳይውል አርብ ተሰቀለ፤

በረከታቸው ይደርብን።
ስንክሳር፤ የቤተክርስቲያን መረጃዎች

No comments:

Post a Comment