Thursday, April 4, 2013

መጋቢት 26 ቀን


በዚች ዕለት የክብር ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የደቀ መዛሙርቱን እግር አጠበ፡፡
የሐዲስ ኪዳንን የቁርባን ሥርዓት ሠርቶ አሳያቸዉ፡፡
በዚህች ዕለትም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ይሁዳ ለአይሁድ በሠላሳ ብር አሳልፎ የሠጠበት ዕለት ነዉ፡፡
በዮሐ 13 ፡ 12 ‹‹‹‹እግራቸዉንም አጥቦ ልብሱንም አንስቶ ዳግመኛ ተቀመጠ ፣ እንዲህ አላቸዉ ፡-ያደረግሁላችሁን ታስተዉላላችሁን ; እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ፡፡እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ እናንተ ደግሞ ለባልንጀሪቻቸችሁ እንዲሁ አድርጉ አለ››› መምህረ ትህትና አምላከ ምህረት ኢየሱስ ክርስቶስ ፡፡ቸርነቱ ይቅርታዉ አይለየን አሜን፡፡

No comments:

Post a Comment