በዛሬዋ ቀን በዴሰተ ጋግራን የተዋህዶ አምድ ወደቀ፤ ይህም አባ ዲዮስቆርስ ነው። የእስክንድርያ 25ኛ ሊቀ ጳጳስ ነው። በሮም ነግሶ የነበረው ፓፓ ሊዮን አንድ ኑፋቄ አመጣ ሁለት ባሕርይ አንድ አካል የሚል በዚያን ወቅት በሮም ነግሰው የነበሩት መርቅያኖስና ሚስቱ ንግስት ብርክያል በዚህ ኑፋቄ ተስማምተው ነበርና በኬልቄዶን ጉባዬ እንዲካሄድ አደረጉ 636 ጳጳሳትና ኤጲስ ቆጶሳት በጉባዬው ተገኙ ዲዮስቆሮስም ተገኘ ሁለት ባህርይ የሚለውን የልዮንን ጦመማር ሰጡት እዘው ጉባይው ፊት ቀደደው ሐዋርያት የመሰረቱት 318ቱ ሊቃውንት የደነገጉት ወልድ ወህድ አንድ አካል አንድ ባህርይ ብለው ነው፤ አንድ አካል ያለው ሁለት ባህርይ የለም ብሎ ከመጽሐፍ እየጠቀሰ አስረዳቸው በነፍስና በስጋ በብረትና በእሳት እየመሰለ አስረዳቸው፤መልስ የሚሰጠው ግን አልነበረም ሁሉም ዝም አሉ፤ አውግዘንሃል ከጉባዬ ውጣልን ብልው አስወጡት። ንግስት ብርክልያ ጉባይው ውሎ እንዴት ነበር ብላ ጠየቀች፤ ሁሉም ሲስማማ ዲዮስቆሮስ ግን አምጾብናል ብለው ነገሮዋት፤ ጥሩልኝ እኔ እመክረዋለሁ አለች አቀረቡላት፤ ለማግባባት ሞከረች ንጉስ የወደደውን ዘመን የወለደውን ተቀብለህ ኑር፤ እምቢ የምትል ከሆነ ግን እናቴ ዮሐንስ አፈወር እንዲሰቃይ እንዳደረች አንተም እንደሱ ትሰቃያለህ አለችው፤ዲዮስቆሮስ ሳቀባት ዮሐንስ አፈወርቅስ የክብር ሞት ሞተ እናትሽ ግን እስካሁን በደይን ትሰቃያለች አላት፤ በዚህ ተቆጥታ አስደበደበችው ጥርሱን አወለቁ ጽህሙን ነጩት፤ የወለቀ ጥርሱን የተነጨ ጽህሙን በፖስታ አድርጎ ዝንቱ ውእቱ ፍሬ ሃይማኖት ይህ የሃይማኖት ፍሬ ነው ብሎ እስክንድርያ ለሚገኙ ምዕመናን ላከላቸው ጥርሱ እንደ ፋና እያበራ ይጠቀሙበት ነበር፤ ከዚህ በኃላ 636ቱ በሙሉ ሁለት ባህርይ ብለው መዝገብ ላይ ፈረሙ ዲዮስቆሮስን ወደ ጋግራን ደሴት በግዞት ይልኩታል እዛ እንደደረሰ ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አደረገ በዚያ ደሴት ያሉ ነዋሪዎች አከበሩት ከፍ ከፍም አደረጉት፤ እርሱም በዚያ ደሴት አምስት ድርሳናትን የጻፈ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ህብስቱ ተለውጦ ስጋ ወልደ እግዚያብሔር ጽዋው ተለውጦ ደመ ወልደ እግዚያብሐር የሚሆንበት ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ አንዱ ነው፤ ይህንን አባት ቤተክርስቲያን እምደ ሀይማኖት ብላ ሰይማዋለች በዛሬዋ ቀን በዛው በግዞት ባለበት በጋግራን ደሴት አረፈ። በረከቱ ይደርብን።
LIKE >>>
https://www.facebook.com/pages/ተዋህዶ-ሀይማኖታችን/117298008428339?ref=hl
No comments:
Post a Comment