Wednesday, September 25, 2013

መስከረም 11

በዚህች ቀን ከሮም ከነገስታት ወገን የሆነ ቅዱስ ፋሲለደስ መንግስቱን ክብሩን ትቶ በሰማዕትነት ሞተ።ታሪኩ እንዲህ ነው የሮሙ ንጉስ ኑማርዮስ በውጊያ ሞተ፤ ሮም የሚመራት የሌላት ሆነች፤መኳንንቱ ተሰባስበው ከላይኛው ግብጽ ስሙ አግሪጳዳ የሚባል የፍየሎች እረኛ የሆነ አንድ ሰው አገኙ ኃይለኛና ብርቱ ነበር ባልደራስ አድርገው ሾሙት፤ ከንጉስ ኑማርዮስ ሴት ልጆች አንዲቷ ተመለከተችው፤ ወደደችው አገባችው፤ ስሙንም ዲዮቅልጥያኖስ ብላ አነገሰችው።ከጥቂት ቀናት በኃላ አብያተ ጣኦታት ይከፈቱ አብያተ ክርስቲያናት ይዘጉ ብሎ አዋጀ ነገረ፤ ክርስቲያኖችንም ማሳደድ ጀመረ፤ የፋሲለደስ ልጆች እጅግ ጀብደኞች ነበሩ ዲዮቅልጥያኖስን ሊገድሉት አሰቡ ፋሲለደስ ግን ከለከላቸው ይልቁን በሰማዕትነት ለመሞት እንደተዘጋጀ ነገራቸው፤ ክብር ይግባውና በዲዮቅልጥያኖስ ፊት ቆሞ በጌታችን በእየሱስ ክርስቶስ ስም ታመነ፤ ዲዮቅልጥያኖስ ግን እጅግ ደነገጠ ምክንያቱም ፋሲለደስ ህዝብ የሚወደው ጀግና ከነገስታት ወገን ነበርና፤ ስለዚህም በስውር ወደ ግብጽ ላከው እዚያም እንደደረሰ መኮንኑ ተቀብሎ በርካታ መከራዎችን አደረሰበ በመንኩራኩር፤ በተሳሉ የብረት ዘንጎች፤ በብረት ምጣድ በብረት አልጋ እስተኝተው ከስሩ እሳት አነደዱበት ሌሎች ዘግናኝ መከራዎችን አጸኑበት ሁለት ጊዜ ሞቶ ሁለት ጊዜም ተነሳ በመጨረሻም በዛሬዋ ቀን አንገቱን በሰይፍ ቆረጡት የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ፤ ይህ ሰማእት በአገራችን በስሙ በርካታ አብያተክርስቲያናት 3 ታላላቅ ገዳማት አሉት። በረከቱ ይደርብን። የመስከረም 11 ስንክሳር፤የቅዱሳን ታሪክ
/117298008428339?ref=hl
 

No comments:

Post a Comment