Wednesday, September 11, 2013

መስከረም 1


መስከረም 1 ቀን ብዙ ተደራራቢ እና ታላላቅ በዓላትን ነው አክብረን የምንውለው:: ቀዳሚው ዘመን መለወጫ;

2.ሊቀ መላእክት ቅዱስ ራጉኤል በዓለ ሲመቱ ነው:: ራጉኤል ማለት መጋቤ ብርሃናት ማለት ነው; ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ነው:: ለሰው ልጅ ምህረትንና ቸርነትን የሚለምንና ዲያቢሎስን ከነሠራዊቱ የሚበቀል መልአክ ነው:: ሄኖ 6:3;::

3.መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐን ከአምላኩ ዘንድ ለእኛ ድኅነት ይሆነን ዘንድ የማይታበል ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን የተቀበለበት::


4.ጻድቁ ኢዮብ ከደረሰበት ፈተናና መከራ በእግዚአብሔር ቸርነት የተፈወሰበት ዕለት ነው::

5. ከ 12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት መካከል አንዱ የሆነው ቅዱስ በርተሎሜዎስ ያረፈበት ዕለት ነው::በርተሎሜዎስ ማለት አትክልተኛ ማለት ነው:: ማቴ ሐዋ ሀገረ ስብከቱ አልዋህ ነው; በሚያስተምርበትም ጊዜ ብዙ ተአምራትን አድርጏል:. አንድ ቀንም በነግህ ወይን ተክሎ ዕለቱን ለመስዋዕት አድርሷል አትክልተኛ መባሉ ቅሉ ለዚህ ነው:: አምላካችን ከቅዱሳኑ ሁሉ ረድኤታቸውንና በረከታቸውን ያሳድርብን:: ለበለጠ መረጃ ሥንክሳር ዘመስከረም 1 እና መዝገ በታሪክ ቁጥር 1 ይመልከቱ::

No comments:

Post a Comment