የሊቀ ዲያቆናት የቀዳሚ ሰማዕት የቅዱስ እስጢፋኖስ ዓመታዊ በዓሉ ነው። ይህም ስጋው የፈለሰበት ነው፤ ነገር ግን አባቶች ባዘዙት መሰረት መስከረም 17 ከመስቀል በዓል ጋር ታቦተ ህጉ ወጥቶ አብሮ ተከብሮ ይውላል። ጥር 1 የእረፍት ቀኑ ነው፤ የተወለደውም በዚሁ ቀን ነው፤ ጥቅምት 17 የተሾመበት ቀን ነው፤ በዓመት እነዚሀ 3ቱ ቀናት ሰማዕቱ በሰፊው የሚዘከርባቸው ቀናት ናቸው። አይሁድ አማጽያን ሰማዕቱን ከገደሉት ከ 300 ዓመት በኃላ እለእስክንድሮስ የሚባል አገሩ ቆስጠንጥንያ ነዋሪነቱ እየሩሳሌም ያደረገ ደገኛ ክርስቲያን በህልሙ ቅዱስ እስጠፋኖስ ተገልጾ ስጋውን እንዲያፈልስ ደጋግሞ ይነግረዋል፤ ስጋውን አስቆፍሮ አስወጣ በዘህም ጊዜ ነፍስን የሚያለመልም ደስ የሚያሰኝ መዓዛ አካባቢውን አወደው፤ በዚህ አላበቃም "ስብሐት ለእግዚያብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰብ" እያሉ መለአክት ሲዘምሩ ተሰማ በአካባቢው የነበረው ህዝብ ሰምቶ ተደነቀ፤ ከስጋው ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራት ተደረጉ አይነስውራን አዩ ጎባጦች ቀኑ ለምጻሞችም ነጹ።ከዚህ በኃላ በዚያው በእየሩሳሌም ታላቅ ቤተክርስቲያን አነጹለት ስጋውን በክብር አሳረፉት። ከዓመታት በኃላ በድጋሚ ስጋው ወደ ቆስጠንጥንያ ሄዷል ለዚህም የሚያስገርም ሰፊ ታሪክ አለው። ከሰማዕቱ በረከት ያድለን።
LIKE >>> https://www.facebook.com/pages/ተዋህዶ-ሀይማኖታችን/117298008428339?ref=hl
No comments:
Post a Comment