Sunday, September 1, 2013

ነሐሴ 26


በዚህች ቀን የአባታችን የአብርሃም ሚስት የተመሰገነች ንጽህት ሳራ አረፈች። የሳራን ገድል በሚያትተው በቅዱስ ኤፍሬም ድርሳን ላይ ሳራ በውበቷ በምድር ከሚኖሩ ሴቶች እንደምትበልጥ ፤ በመከራ ወራት እንደወጣች የጸሐይን ጮራ መስሏት ይናገራል። በሰደታቸው ወቅት የጌራራው ንጉስ አቤሜሌክ ሊያገባት ባሰበ ጊዜ፤የታዘዘ መልአክ መጣ ልብሱ የሚንበለበል እሳት ይመስላል ጎኑን መታው በግንባሩም ፍግም ብሎ ወደቀ እንደ በድንም ሆነ መናገርም ተሳነው፤ሲነጋም መኳንንቱ መሳፍንቱ ሊጠይቁት ቢመጡ ወድቆ አገኙት፤ጦርነት ሳትገጥም ማነው የጣለህ አሉት ? እርሱ ግን በምልክት አብርሃምን እንዲጠሩለት ነገራቸው፤አብርሃምን ጠሩለት ጸልዮም አዳነው፡፡በሳራ ምክንያት የአገሩ ሁሉ ሴቶች ማህጸን ተዘግቶ ነበር ይላል፤ በኋላም በእርሷና በአብርሃም ምልጃ መውለድ ችለዋል፡፡ ዘፍ 20፤17። ሳራ የ 90 አብርሃም የ 100 ዓመት ሽማግሌዎች ሆነው ይስሃቅን ወለዱት። ይስሃቅ አደጎ ከእስማኤል ጋር ሲጫወት ሳራ አየችው አብርሃምንም እንዲህ አለችው፤ይህችን ባሪያ ከነልጇ አባራት የባሪያ ልጅ ከልጄ ጋር አይወርስምና ይህም ነገር ለአብርሃም ጭንቅ ሆነበት እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው። ስለ ባሪያህና ስለ ብላቴናው አትዘን፤ ሣራም የምትነግርህን ቃል ሁሉ ስማ፤ በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃልና። የባሪያይቱን ልጅ ደግሞ ሕዝብ አደርገዋለሁ፥ ዘርህ ነውና።ዘፍ 21፤9 ይህ እጅግ ድንቅ ሚስጢር አለው፤ቅዱስ ጳውሎስ በገላትያ መልዕክቱ ሳራን የቤተክርስቲያን ምሳሌ አድርጓታል። ሳራ በዚህ ምድር 127 ዓመት ኖረች ነሐሴ 26 ቀን አረፈች፤ አብርሃም በኬብሮን ቀበራት። በረከቷ ይድርብን ፡፡

LIKE >>> https://www.facebook.com/pages/ተዋህዶ-ሀይማኖታችን/117298008428339?ref=hl

No comments:

Post a Comment