Thursday, December 13, 2012

ታህሳስ 5



በዚህች ቀን ቅድስት አውጋንያ አረፈች፤ አገሯ እስክንድርያ ነው አባቷ አገር ገዢ ነበር ፊሊጶስ ይባላል ጣኦት አምላኪ ነው እናቷ ግን ደግ ክርስቲያን ነበረች በድብቅ ክርስትናን አስተማረቻት ስታድግ ታላላቅ መኳንንቶች አጯት እርሷ ግን ጠፍታ ወደ አባ ቴዎድሮስ ገዳም ገባች መነኮሰች ማንም ሰው እንዳያውቃት ፍጹም ወንድ መሰለች ስሟንም አባ አውጋንዮስ አሰኘች፤ አባቷ ጠፍታ መቅረቷን ባወቀ ጊዜ መሪር ለቅሶ አለቀሰ እሷን የሚመስል ጣኦት አስቀርጾ ማምለክ ጀመረ። ከአንድ ዓመት በኃላ ትጋቷን አይተው መነኮሳቱ የገዳሙ አበምኔት አድርገው ሾሟት፤ (አበምኔት ለወንድ እንደሆነ ልብ ይሏል) እግዚያብሔር በሰይጣና...ትና በድውያን ላይ ፍጹም ስልጣን ሰጣት ከብዙ አገር በሽተኞች እየመጡ በእጇ ይፈወሱ ነበር፤ ከእለታት አንደ ቀን ግን እንዲህ ሆነ አንዲት ሴት ቅድስት አውጋንያን ባየቻት ጊዜ ወንድ መስላት ፍጹም ወደደቻት፤ ምንኩስናህን ትተህ ባል ሆነከኝ ከኔ ጋር ኑር አለቻት፤ ሂድ አንተ ሰይጣን ብላ አባረረቻት፤ ባሳፈረቻት ጊዜ ወደ አገር ገዢው ሄዳ በዚያ ገዳም የሚኖር መነኩሴ ሊደፍረኝ ሲል አምልጬ መጣሁኝ አለችው፤ ዘፍጥረት 39 14 መኮንኑ በሰማ ጊዜ ተቆጣ ሁሉንም መነኮሳት ታስረው እንዲሰቃዩም አደረገ፤ የሞቱም አሉ፤ ቅድስት አውጋንያ ስቃያቸውን ባየች ጊዜ መኮንኑን ጌታዬ እውነቱን እነግርሃለው የምፈልገውን ነገር ግን አትከልክለኝ አለችው፤ አስማለችውም፤ ከዚያም ልጁ አውጋንያ እንደሆነች ገለጸችለት፤ አንገቷን አቅፎ አለቀሰ፤ እኔም ባንቺ አምላክ አምናለው አላት ከነቤተሰቦቹም ተጠመቀ የበቃ ታላቅ አባት እስከመሆን ደርሶ በሰማእትነት ነው የሞተው እርሷም ወደ ሮም ሄዳ የገዳም እመምኔት ሆና ለብዙ ዘመናት ለረጅም ወራት በተጋድሎ ኖራ ታህሳስ በባተ በአምስተኛው ቀን አረፈች፤ በረከቷ ይደርብን ከጻድቁ አቡዬ በረከታቸውንም ያሳትፈን።

No comments:

Post a Comment