Tuesday, December 11, 2012

ታህሳስ 1


++ዘአጽናእኮሙ ለእሙንቱ አበዊነ ለሄኖክ ወኤልያስ አንተ አፅንአነ በመንፈስ ቅዱስ++   
እነሆ የተባረከ የታህሳስ ወር ባተ፤ ይህ ወር ቀኑ 9 ሰዓት ነው ሌሊቱ 15 ሰዓት፤ ቀኑ በጣም አጭር ነው ቶሎ ይመሻል ሌሊቱ በጣም ረጅም ነው፤ ታህሳስ 1 በዚህች ቀን  በገለዓድ ይኖር የነበረው ቴስብያዊው ኤልያስ  የተወለደበት ቀን ነው፤ ታሪኩ 1 ነገስት 171 ላይ በስፋት ይገኛል፤ በእሳት ሰረገላ የተሰወረው ጥር 6 ቀን ነው፤ እነዚህን ሁለት ቀናት ቤተክርስቲያን ነብዩን አስባ ትውላለች፤ ይህ ነብይ በአገራችን በስሙ የታነጹለት አብያተክርስቲያናት አሉት ከነዚህም  በመዲናችን አዲስ አበባ ርዕሰ አድባራት እንጦጦ ደብረ ሐይል ቅዱስ ራጉኤል ወኤልያስ ቤተ ክርስቲያን የሚገኘው ቤተክርስቲያን አንዱ ነው፤ ኤርትራ ውስጥም አንድ ቤተክርስቲያን አለው፤ ዛሬ በደማቁ ተከብሮ ይውላል፡፡ አክአብና ኤልዛቤል ምሰኪኑን ናቡቴ ከአባቶቹ  እርስት አፈናቅለው በግፍ  በገደሉት ጊዜ፤ ንጉሱን ሳይፈራና ሳያፍር በግልጽ የዘለፈ ነብይ ነው፤ ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይንም የለጎመ ነው ይህንንም  ያዕቆብ በመልእክቱ እንዲህ ሲል መስክሯል ያዕ  5 16   "የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች። ኤልያስ እንደ እኛ የሆነ ሰው ነበረ፥ ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፥ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም፤ ሁለተኛም ጸለየ፥ ሰማዩም ዝናብን ሰጠ ምድሪቱም ፍሬዋን አበቀለች"

ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን፡፡

No comments:

Post a Comment