Wednesday, December 12, 2012

ታህሳስ 4


በዚህች ቀን የሊቀ ሐዋርያት የቅዱስ ጴጥሮስ ወንድም የተመሰገነ ቅዱስ እንድርያስ በሰማዕትነት አረፈ፤ የዚህ ሐዋርያ ቁጥሩ 12 ሐዋርያት ነው፤ ማቴ 4 18 ቀድሞ በገሊላ ባህር ማዶ በቤተሳይዳ ዓሳ አጥማጅ ነበር፤ ሰውን ታጠምዳለህ ብሎ ጌታ ጠራው ተከተለው። ዓለምን ዞረው ለማስተማር ዕጣ ሲያወጡ ለቅዱስ እንድርያስ ልዳ ደረሰችው ልዳ ማለት የቅዱስ ጊዮርጊስ አገር ናት፤ ሊያስተምር ወደዚያች አገር ገባ፤ ጣኦት አምላኪዎች ወሬውን ሰምተው ሊጣሉት ሾተል ይዘው ወጡ፤ ሐዋርያው እንድርያስ ግን ከፍ ካለ ቦታ ላይ ቆሞ እንዲህ ሲል ሰበከ " የአህዛብ ጣኦታት የሰው እጅ ስራ ናቸው ዓይን አላቸው አያዩም፤ ...ጆሮ አላቸው አይሰሙም፤ አፍንጫ አላቸው አያሸቱም፤ እጅ አላቸው አይዳስሱም፤ እግር አላቸው አይሄዱም በጉሮሮአቸውም አይናገሩም የሚሰሯቸው የሚያምኑባቸው ሁሉ እንደ እነርሱ ይሆናሉ፤ መዳን በእግዚያብሔር ነው እርሱም እየሱስ ክርስቶስ ነው እያለ ሰበከከቃሉ ጣዕም ከአንደበቱን ቅልጥፍና ከነገሩ ማማር የተነሳ የወገባቸው ትጥቅ ተፈታ ሾተላቸውን ጣሉ፤ በጌታችን አምነው ተጠመቁ ይላል። ይህ ሐዋርያ በሰው ቋንቋ የምትናገር የምትላላከው እርግብ ነበረች፤ ተረፈ ኤርሚያስ 1024 ዘፍጥረት 8 8 በነዚህ ጥቅሶች ኖህ ከርግብ ባሮክ ከንስር ጋር በሰው ቋንቋ ሲነጋገሩ ሲላላኳቸውም እናያለን፤ ሐዋርያው እንድርያስ ከእርግብ ጋር ሲነጋገር ህዝቡ ይገረም ነበር። ይህ ሐዋርያ በዛሬዋ እለት ግብራቸው እጅግ ወደ ከፋ አገረ ሰዎች ገብቶ ሲያስተምር አሰቃይተው ገድለውታል። በረከቱ ይደርብን

No comments:

Post a Comment