Tuesday, December 11, 2012

ታህሳስ 3



 
 
እመቤታችን 3 ዓመት ሲሆናት ጡት አቆመች አባባ እማማ እያለችም መጫወት ጀመረች በዚህን ጊዜ ቅድስት ሐና ለባሏ ጌታዬ ልጃችን አድጋለች በተሳልነው መሰረት ለቤተ እግዚያብሔር እንስጣት አለችው፤ ይዘዋት ወደ ቤተመቅደስ ሲሄዱ ካህኑ ዘካርያስ ጉባዬ ዘርግቶ ህዝቡን ሰብስቦ እያስተማራቸው ነበር፤ እመቤታችንን ቢያያት ከጸሐይ አብርት ከመብረቅ አስፈርታ ታየችው፤ ይህችን የመሰለች ፍጡር ምን ልንመግባት ነው ብለው ተጨነቁ፤ በዚህ ጊዜ መልአኩ  ፋኑኤል ህብስት ሰማያዊ ጽዋ ሰማያዊ ይዞ ተገለጸ አንድ ክንፉን ጋርዶ አንድ ክንፉን አጎናጽፎ ከመሬት አንድ ክንድ ከስንዝር ከፍ አድርጎ ህብስቱን አብልቶ ወይኑን አጠጥቶ እመቤቴ ንገድ ባስመታሁሽ ማሪኝ ብሎ አርጓል፤ ይህ የሆነው በታህሳስ 3 ነው።  
አቡነ ዜና ማርቆስን ጣኦት አምላኪው ልባቸውን በጦር በወጋቸው ጊዜ በደም ፈንታ ብረሃን እንደፈሰሰ

ዳግመኛ በዛሬ ቀን ታላቁ ኢትዮጰያዊው ቅዱስ አቡነ ዜና ማርቆስ አረፉ፤ የተክልዬ አጎት ናቸው ትውልዳቸው ሸዋ ቡልጋ ነው በዚያ ታላቅ ገዳም አላቸው ዛሬ በደማቁ ተከብረው ይውላሉ፤ ጉራጌ አገር የሚገኘውን ታላቁን የምዑር ገዳም የመሰረቱት እኚሁ አባት ናቸው፤ ከዚህ ያለው ስዕል አቡነ ዜና ማርቆስን ጣኦት አምላኪው ልባቸውን በጦር በወጋቸው ጊዜ በደም ፈንታ ብረሃን እንደፈሰሰ የሚያሳይ ነው። ሌላው በዛሬዋ ቀን የሚከበረው እመቤታችንን መና እየመገበ ያሳደጋት ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ፋኑኤል ነው። እመቤታችንን ከሐና ማህጸን ፈጥሮ ከፍጥረተ ዓለም ለይቶ ከሁሉ አልቆ የእናት አማላጅ ትሁናችሁ ብሎ የሰጠን እግዚያብሔር ይመስገን፤ ከበዓሉም በረከት ያሳትፈን።

No comments:

Post a Comment