Thursday, February 21, 2013

ጥር 28

በዚህች ቀን የማኀው ልጅ ዮሴፍ አረፈ። የዚህ ጻድቅ ወላጆቹ ሰቃልያነ ክርስቶስ አይሁዳዊ ናቸው። በልጅነቱ አባቱን ተደብቆ ከሰፈሩ ልጆች ሀጻናት ጋር የቤተክርስቲያንን መጽሐፍት አጠና ቤተክርስቲያንም እየሄደ ይቆርብ ነበር። አባቱ ይህን በሰማ ጊዜ ተቆጣ እጅና እግሩን አስሮ የእሳት ጉድጓድ ውስጥ ወረወረው የእቶኑንም በር ዘጋበት ''አባትና እናቴ ተዉኝ እግዚያብሔር ግን ተቀበለኝአይደል ያለው ዳዊት መዝ 2710 እናቱ ልጇን በጣችው ጊዜ አለቀሰች መንደሩ ሁሉ ተሸበረ፤ ከሰባት ቀን በኃላ ወደ እሳት እንደተጨመረ ተሰማ እያለቀሱ ወደ ጉድጓዱ መጡ የዮሴፍን ድምጽ ከውስጥ ሰሙትወንድሞቼ አታልቅሱ ...እመቤታችን እርዳታ በህይወት አለው አላቸው፤ ሊቀ ጳጳሱ ተጠራ ካህናት መስቀል ጥና ይዘው መጡ ጸሎት አድርሰው ከጉድጓድ አወጡት፤ ከራሱ ጸጉር አንዲቷ እንኳን አልተቃጠለችም ዳን 3 25 አባቱ ይህን ተአምር ባየ ጊዜ ሊቀ ጳጳሱ እግር ስር ወድቆ አለቀሰ በክርስቶስም አምኖ ተጠመቀ። ዮሴፍ ግን ወደ ገዳም ገባ 28 ዓመት በተጋድሎ ኖረ በየሰባት ቀኑ አንዴ ነበር የሚቀምሰው፤የእረፍት ቀኑ ሲደርስ የእመቤታችን ስዕል ጋር ቆሞ ረጅም ጸሎት አደረገ፤ እመቤታችን ተገልጻ ልጄ ዮሴፍ 3 ቀን በኃላ 3 ሰዓት ወደ እኔ እወስድሃለው አለችው በዚያው ባለችው ቀንና ሰዓት በክብር አረፈ ይህም ጥር 28 ነው። ልመናዋ ክብሯ የልጇ የወዳጇ ቸርነት ከሁላችን ጋር ይሁን፤ከዮሴፍም በረከት ያሳትፈን። ይህ ታሪክ ስንክሳር ላይና ታምረ ማርያም ላይ ይገኛል። ዳግመኛም በዛሬዋ ቀን 5 ነገስታት ከአገር አገር እየተቀባበሉ መከራ ያጸኑበት የታላቁ ሰማዕት የቀሌምንጦስ የእርፍት ቀኑ ነው በረከቱ ይደርብን።

No comments:

Post a Comment