Friday, February 1, 2013

ጥር 24



 
የኢትዮያዊው ጻድቅ ብጹእ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ስባረ አፅማቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በታላቅ ድምቀት አክብራ የምትውልበት ታላቅ ቀን ነው።አባታችን ኢትዮጵያዊው ፃድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት 22 ዓመታት ደብረ ሊባኖስ በሚገኘው ደብረ አሰቦ ዋሻ ውስጥ ሲፀልዩ ከመቆም ብዛትም እግራቸውን አጥተዋል። ለዓመታት ከቆሙበት ሳይቀመጡ ከፊት ከኋላ ከጐን እና ከጐን ምንም ሳይደገፉ በአንድ ቦታ በመወሰን 22 ዓመታት ደብረ ሊባኖስ በሚገኘው ደብረ አስቦ ዋሻ ውስጥ ሲፀልዩ ከመቆም ብዛትም እግራቸውን አጥተዋል። ከዚያም 7 ዓመታት በአንድ እግራቸው ቆመው ፀሎታቸውን ቀጠሉ። ስለ ክብራቸውም ከእግዚአብሔር ክንፍ ተሰጥቷቸዋል። በአጠቃላይ 29 ዓመታት በጸሎት ቆይተዋል።
ዕረፍታቸውም በተወለዱ 99 ዓመት ሲሆን ቀኑም ነሐሴ 24 ቀን ነው።
በዚህም መሠረት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን ለዕረፍታቸው በእግዚአብሔር ፊት ለከበረና ብዙ ክብር ለተሰጣቸው አባታችን በየዓመቱ ነሐሴ 24 ቀን በዓለ ዕረፍታቸውን ታህሳስ 24 ቀን በዓለ ልደታቸውን ዛሬ ጥር 24 ደግሞ ስባረ አፅማቸውን በታላቅ ድምቀት ታከብራለች።የአባታችን የፃድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ጸሎታቸው እና አማላጅነታቸው ቤተክርስቲያናችንን አገራችንን ኢትዮጵያን እና እኛን ህዝቦቿን ከፈተና ይጠብቀን ዘንድ በቃልኪዳናቸው ያስቧት አሜን!!!

No comments:

Post a Comment