Sunday, January 13, 2013

ጥር 4



እንኳን ለወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ በአል አደረሰን በዚህች ቀን ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ሞትን ሳይቀምስ የተሰወረበት ቀን ነው፤ ዮሐ 21 20 ቅዱስ ዮሐንስ ብዙ ስሞች አሉት ፍቁረ እግዚ፤ታኦሎጎስ ( ነባቤ መለኮት ማለት ነው በአማርኛው ደግሞ ስለመለኮት የሚናገር ማለት ነው፤ ከአባቶቹ ነብያት ከወንድሞቹ ሐዋርያት መካከል እንደ ቅዱስ ዮሐንስ ሚስጥረ ስላሴን አምልቶ አስፍቶ የተናገረ የለም፤ሌላ ስሙ አቡቀለምሲስ ይባላል ባለ ራዕይ የራዕይ አባት ማለት ነው፤ቁጽረ ገጽም ይባላ የጌታችንን ስቃዩን ካየ በኃላ ፊቱ ሳይፈታ 70 ዓመት ሙሉ አልቅሷል፤ ከመስቀል ስር ያልተለየው ብቸኛው ሐዋርያ ቅዱስ ዮሐንስ ነው፤ እመቤታችንን በአደራ የተቀበለ በእንድ ቤት ልጅ ሆኗት 15 ዓመት የኖረ ይህ ሐዋርያ ነው፤ መልኩ ጌታችንን ይመስል ነበር፤ ለዚህም ነው ይሁዳ ጌታን በመሳም ለአይሁድ አሳልፎ የሰጠው መልካቸው ስለሚመሳሰል ተሳስተው ዮሐንስን እንዳይዙት፤ ስለዚህ ሐዋርያት ስንቱን እንናገር ብዙ መከራ ተቀብሏል ነገር ግን እንደ ወንድሞቹ ሐዋርያት ደሙ ፈሶ በሰማዕትነት አይደለም የሞተው፤ 90 ዓመቱ በዛሬዋ ቀን ከነስጋው ተሰወረ እንጂ በረከቱ ይደርብን። "በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። ...ቃልም ስጋ ሆነ" ይህን ቃል ያነበበ ሰው ግን እንዴት ይስታል፤ "አቤቱ ምሳሌ ስጠኝ እንጂ ምሳሌ አታድርገኝ" የምትለዋ ጸሎት እንዴት መልካም ነች፤ ወደ ነገራችን እንመለስ፤  በነገራችን ላይ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌሉን የጻፈው በኤፌሶን ነው ዘመኑ መቼ ነው ቢሉ ጌታ ባረገ 30 ዓመቱ፤ የጻፈበት ቋንቋ ጽርዕ ይባላል፤ እናም ወንጌሉን ሲጀምር በመጀመሪያ ቃል ነበር ብሎ መጻፍ ሲጀምር ራዕይ ያያል ከዋንኞቹ መልአክት አንዱ  ከትልቅ ሐይቅ ዳር ቁጭ ብሎ  የሐይቁን ውኃ  በእንቁላል ቅርፊት እየጨለፈ ወደ መሬት ያፈሳል ቅዱስ ዮሐንስ ጠጋ ብሎ ምን እየሰራህ ነው ይለዋል የሐይቁን ውኃ ወደ መሬት እፍስሼ ለመጨረስ ነው ይለዋል ይህ እንዴት ይሆናል ደግሞም በእንቁላል ቅርፊት ይለዋል፤ ይህ ሐይቅ ፍጡር ነው ከረጅም ዘመን በኃላ ሊሳካሊኝ ይችላል አንተስ አለክ አይደል ቢቀዱት የማያልቀውን ቢጀምሩት የማይጨርሱትን የመለኮት ነገር የምትመራመር አለው በዚህ ጊዜ ነው የሐንስ የጀመረውን አቁሞ  ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን። ብሎ ወደ ሚስጢረ ስጋዌ የገባው ዮሐ 114

ዮሐንስ ወንጌላዊ

ዮሐንስ ማለት ‹‹ የእግዚአንሔር ጸጋ ነዉ››፤ደስታ ማለት ነዉ፡፡አባቱ ዘብዴዮስ እናቱ ማርያም ባዉፍልያ ትባላለች፡፡ቁጥሩ ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት የሆነ ያዕቆብ የተባለ ወንድም ነበረዉ፡፡ ማቴ 421 ማር 120 ፤ማቴ 2020 ቅዱስ ዮሐንስ አስቀድሞ የዮሐንስ መጥምቅም ደቀ መዝሙር ነበር፡፡ ዮሐ 1 35 ቅዱስ ዮሐንስ ከአባቱና ከወንድሙ ጋር ዓሣ በሚያጠምድበት በገሊላ ባህር ላይ መረቡን ሲያበጅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያነት ጠራዉ፡፡ እሱም አባቱን ሌሎቹንና ታንኳን ትቶ ከወንድሙ ያዕቆብ ጋር ጌታን ተከተለዉ፡፡
የዮሐንስ ስሞች
1-
-
ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ 2--ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ
3--
ዮሐንስ ቁጽረ ገጽ 4--ዮሐንስ ታኦሎጎስ
5--
ዮሐንስ አቡቀለምሲስ 6--ዮሐንስ ወንጌላዊ 7--ዮሐንስ ዘንስር
1----
ቅዱስ ዮሐንስ ወንድሙ ያዕቆብ የሰማርያ ሰዎች በእሳት እንዲጠፋ ተመኝተዉ ነበር ፡፡በዚህ ዓይነት የችኩልነት ስሜታቸዉ የተነሳ ጌታ ‹‹‹ቦአኔርጌስ››‹‹‹‹የነጎድጓድ ልጆች›››››ብሏቸዋል፡፡ማር 317 ሉቃ 954 በምሥጢር ደቂቀ ምሥጢር ደቂቀ መለኮት ሲል ነዉ፡፡ማር 317
2----
ለጌታ በጣም ቀራቢ ከነበሩት ሦስት የምሥጢር ሐዋርያት ( ጴጥሮስ ፤ያዕቆብ ዮሐንስ )ቀዳሚዉ ነዉ፡፡ጌታችን ምሥጢረ ተአምራትን በኢያኢሮስ ቤት ምሥጢረ መንግስትን(መለኮትን) በደብረ ታቦር ምሥጢረ ምጽአትን በደብረ ዘይት ምሥጢረ ጸሎትን በጌቴ ሴማኒ ሲገልጽና ሲያሳይ አብሮ የተመለከተ በመሆኑና ለጌታ በጣም ቀራቢ በመሆኑና በወንጌልም ‹‹ጌታ ይወደዉ የነበረ ደቀ መዝሙር ››ተብሎ ስለ ተጠቀሰ የጌታ ወዳጅ ፍቁረ እግዚእ ይባላል፡፡ዮሐ 13 23 ፡፡
3---
ቅዱስ ዮሐንስ እስከ መስቀል ድረስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለዉን መከራ በማየቱ ከዚያ ዕለት ጀምሮ 70 ዘመን ሙሉ ፊቱ በኅዘን የተቋጠረ በመሆኑ (ቁጽረ ገጽ) ሆኖ ኖሯል፡፡
4---
ቅዱስ ዮሐንስ ምሥጢረ ሥላሴንና ምሥጢረ ሥጋዌን አምልቶና አስፍቶ በመጻፉ (ታኦጎሎስ) ተብሏል፡፡ትርጉሙም ነባቤ መለኮት (የመለኮትን ነገር የሚናገር)ማለት ነዉ፡፡
5--
ፍጥሞ በምትባል ደሴት ላይም ወደ ፊት የሚሆነዉን ነገር በራእይ ስለተገለጸለት በግሪክ ቋንቋ አቡቀለምሲስ ተብሏል፡፡ትጉሙም የራእይ አባት ማለት ነዉ፡፡
6---
ቅዱስ ዮሐንስ የዮሐንስ ወንጌልን በመጻፉ ወንጌላዊ ተብሏል፡፡
7---
በሥላሴ ስዕል ላይ ካሉት አራቱ እንስሳ አንዱ ንስር ነዉ፡፡ንስር በእግሩ ይሽከረከራል በክንፉ ይበራል፡፡ንስር በእግሩ እንደመሽከርከሩ ቅዱስ ዮሐንስም የክርስቶስን ምድራዊ ታሪኩን ጽፏል፡፡ንስር በክንፉ መጥቆ እንደሚበር ቅዱስ ዮሐንስም ከሌሎቹ ወንጌላዉያን ለየት ብሎ የመለኮትን ሰማያዊ አኗኗር ጽፏል፡፡ንስር አይኑ ንጹህ ነዉ ሽቅብ ወጥቶ ቁልቁል ሲመለከት ቅንጣት የምታክል ሥጋ የታመልጠዉም፡፡ቅዱስ ዮሐንስም ወንጌል ሲጀምር እጅግ ርቆና መጥቆ የሥላሴን አንድነትና ሦስትነት የአካላዊ ቃልን (የእግዚአብሔር ወልድን)በቅድምና መኖር ተናግሯል፡፡በዚህም ዮሐንስ ዘንስር ተብሏል፡፡
ከሐዋርያት መካከል ሞትን ያልቀመሰ በህይወተ ሥጋ እያለ ወደ ሰማይ የተነጠቀ እንደ ሔኖክ ፣እንደ ኤልያስ በብሔረ ሕያዋን የሚኖር ሐዋርያ ነዉ፡፡ጌታችንም ለቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹‹‹ዮሐንስ እኔ እስክመጣ ድረስ በሕይወት ይኖር ዘንድ ብወድስ ምን አግዶህ??›››ዮሐ 2120 ይህም እስከ ምጽአት ድረስ እንደሚኖር መናገሩ ነዉ፡፡በማቴ 1618 ላይ ‹‹እዉነት….……ሞትን የማይቀምሱ አንዳንድ አሉ›››››ያለዉ ቃል ለቅዱስ ዮሐንስና መሰሎቹ የተነገረ ቃል ነዉ፡፡
የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በረከቱ ረድኤቱ ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡

No comments:

Post a Comment