Sunday, January 13, 2013

ጥር 6



ከጌታችን እየሱስ ከርስቶስ ዘጠኙ ንዑሳን በዓላት አንዱና የመጀመሪው ነው፤ ግዝረተ ክርስቶስ ይባላል፤ ሉቃ 1 21   “ሊገርዙት ስምንት ቀን በሞላ ጊዜ፥ በማኅፀን ሳይረገዝ በመልአኩ እንደ ተባለ፥ ስሙ ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ።  እመቤታችን ወደ ግዘረት ቤት ወሰደችው፤ ገራዡ ምላጩን ይዞ ቀረበ ነገር ግን ምላጩ እጁ ላይ ሳላ ውሃ ሆኖ ፈሰሰ፤ ጌታችንም በተአምራት የተገረዘ ሆኖ ተገኘ ይላል፤ ምነዋ ቢባል ጌታችን ደሙ የሚፈሰው ስጋውም  የሚቆረሰው አንዴ በእለተ ዐረብ ብቻ ስለሆነ ነው፡፡ ጌታችን የሰውን ስርዓት ሁሉ ጠብቋል፤ እራሱ እንደተናገረው  እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም። ማቴ 5 17 አምላክ ነኝና እለቱን ተጸንሼ እለቱን ልወለድ አላለም 9 ወር 5 ቀን ቆይቶ ተወለደ እንጂ እንደ ህጻናትም ዋይ ዋይ እያለም አለቀሰ፤ ደግሞም እየው በዛሬዋ ዕለትም ተገረዘ፤ የሚገርም ነው፡፡ መገረዝ ወይም አለመገረዝ ምንም አይጠቅምም ሐዋርያው ጳውሎስ እንደተናገረው፤ ግዝረት የጥምቀት ምሳሌ ነበር በአማናዊው ጥምቀት ተተክቷል፡፡ እርሱ የጥበበኞች ፈጣሪ ሲሆን  ፊደል ሊቆጥር ወደ  ቄስ ትምህርት ቤት የኔታ መምህሩ ጋር ሄዷል፤ መምህሩ አሌፍ በል አለው ጌታም አሌፍ አለ፤ አሌፍ ማለት የዕብራይስጥ ሆሄ ነው እኛ እንደምንለው እነሱ ደግሞ   አሌፍ ቤት ጋሜል  ዳሌጥ    ዋው  ዛይይላሉ፤ አናም ፊደል መቁጠር ጀመረ አሌፍ በል አለው አሌፍ አለ ቤት በል አለው መጀመሪያ የአሌፍን ትርጉም ንገረኝ እንጂ አለው መምህሩ ተናዶ እኔ የምልህን ዝም ብለክ በል አለው ጌታችንም መልሶ የአሌፍን ትርጉም ሳላውቅ ዘልዬ ቤት አልልም አለው ሂድ  ወላጅ ይዘህ አለው እመቤታችንን ይዞ ሄደ እኔ ልጅሽን ማስተማር አልችልም ይዘሽሊኝ ሂጂ አላት መምህሩ የአሌፍን ትርጉም ስለማያውቀው ነው፤ ማለት ሀለዎተ እግዚብሔር መሆኑን ስንቶች መምህራኖች ነግረውን ይሆን ለዚያም ነው እኮ “” ሀሌታዋ ”” የምንለው አጋ-ጣሚ ሆኖ ዛሬ የታላቁ አባት  የኖህ እረፍቱ ነው፤ “”ሐመሩ ”” የምንለው ስያሜውን ያገኘው ከዚሁ ከኖህ መርከብ ነው፤ ሐመር ማለት መርከብ ማለትም አይደል፡ ይህም የእመቤታችን አንድም የቤተክርስቲያን ምሳሌ ነው፤ ጎበዝ መምህራን ፊደል ሲያስቆጥሩ ትርጉሙን ጭምር እየተናገሩ ታሪኩን እያነሱ እያወሱ ያስተምሩ ነበር፤ መምህር ግን ትርጉሙን አያውቅም ነበርና ጌታን ወላጅ አምጣ አለው፤ ልጅሽን ማስተማር አልችልም ከአቅሜ በላይ ነው አለ፤ ሰፊ ታሪኩ ታምረ እየሱስ ላይ ይገኛል፡፡ ሌላው በዛሬዋ ቀን ቴስቢያዊው ነብዩ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ወደ ብሔረ ሕያዋን የተወሰደበት ቀን ነው፤ የዚህ ነብይ ልደቱ ታህሳስ 1 ቀን ነው፤  አዲስ አበባ አንጦጦ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ታቦተ ህጉ አለ ዛሬ በደማቁ ተከብሮ ይውላል፤ ከበዓሉ በረከት ያደሳትፈን፡፡   

                                ኤሊያስ በሰረገላ ወሰደው ደመና
                               ኤሊያስ ያረገው በእሳት ሰረገላ
                               በጾም በጸሎት ነው አይደለም በሌላ    

No comments:

Post a Comment