ተቀብሮ አልቀረም ተገኝቷል መስቀሉ
በዚህች ቀን ክብር ይግባውና የጌታችን የመድሐኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ለዘመናት ተቀብሮ ከኖረበት ቦታ የወጣበት ቀን ነው። መስከረም 16 ቀን ደገኛዋ እናት እሌኒ ቅድስት ደመራ ደምራ በደመራው ጢስ አማካኝነት የተቀበረበትን ቦታ አገኘች መስከረም 17 ቁፋሮ ጀመረች፤ከ 300 ዘመናት በላይ ቆሻሻ እየተጣለበት ታላቅ ተራራ አህሎ ነበርና እነሆ ቁፋሮ ስድስት ወራት ፈጀባቸው መጋቢት 10 በዛሬዋ ቀንም መስቀሉ ወጣ። ሦስት መስቀሎች ናቸው፤ሁለቱ መስቀሎች ሽፍታዎቹ የተሰቀሉባቸው ሲሆኑ አንዱ የጌታችን ነው፤ ታዲያ እንዴት ለየችው ቢሉ የጌታችን መስቀል ታላላቅ ታአምራትን አድርጓል ድውይ ፈውሷል ዓይነስውር አብርቷል። ይህንን ቀን ቅድስት ቤተክርስቲያን "መስቀለ እየሱስ" ስትል ታከብረዋለች፤ በዛሬዋ ቀን ዝማሬው፤ ምስጋናው፤ ትምህርቱ፤ ቅዳሴው ፤ ንባቡ ሁሉም መስቀልን የሚመለከቱ ናቸው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስለ መስቀል የሚጣፍጥ ነገር ተናገረ እንዲህ ሲል “ ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።” ገላትያ 6፤14። ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን።
LIKE OUR PAGE >>>
— with Ayalew Amogne.
ተዋህዶ-ሀይማኖታችን: መጋቢት 10 >>>>> Download Now
ReplyDelete>>>>> Download Full
ተዋህዶ-ሀይማኖታችን: መጋቢት 10 >>>>> Download LINK
>>>>> Download Now
ተዋህዶ-ሀይማኖታችን: መጋቢት 10 >>>>> Download Full
>>>>> Download LINK