...ስት አክሳኒ አልተመለሰችም በመርከብ ተሳፍራ መጀመሪያ ወደ ደሴተ ቆጵሮስ ከዚያም ወደ እስክንድርያ ሄደች በመንገድ ላይ ሳለች ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በራእይ ተገለጸላት የምትሰራውን ሁሉ ነገራት፤ እርሷም ወደ ሊቀ ጳጳሱ ቴዎፍሎስ ገባች ጸጉሯን ላጭቶ አመነኮሳት፤ ከአባቷ ቤት ይዛው ባመጣችው ወርቅ የቅዱስ እስጢፋኖስን ቤተክርስቲያን አሳነጸችበት፤ ምንም ምን ሳትይዝ ከደናግል ገዳም ገባች፤ ከጥሬ ባቄላ በቀር እሳት የነካውን ምግብ አልተመገበችም ማቅ ለብሳ አመድ ነስንሳ በተጋድሎ ኖረች፤በዛሬዋ ቀንም በክብር አረፈች፤ በዚህ በእረፍቷ ቀን ታላቅ የብርሃን መስቀል ስጋዋ ባረፈበት ቦታ ላይ ታየ በዙሪያውም የሚያበሩ ከዋክብትና የክብር አክሊላት ነበሩ መነኮሳቱ ምን ድንቅ ነገር ነው ብለው ሲቀርቡ መሞቷን ተረዱ ገንዘው እስኪቀብሯት ድረስ መስቀሉ ያበራ ነበር ከዚያ በኃላ ተሰውሯል። “ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች፤ በኃጥኣን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ። መዝ 84፤10 በረከቷ ይደርብን።
No comments:
Post a Comment