...ለ ሚዛኑ በግራ በኩል አዘንብሏል በቀኝ በኩል በዶ ነው፤ " ምን ይሻላል ሚዛኑ እኮ ባዶ ነው" አሉ መልአክት ከመካከላቸው አንዱ መልአክ ተነስቶ ይህቺ አንድ እንጀራ አለች እርሷን ላስቀምጣት አላቸው፤ በዚህ ሁሉ ኃጢያቶች ይህቺ ብቻ እንጀራ ምን ትሰራለች አሉት፤ ማቴ 25 ፤ 35 በዚህን ጊዜ ደንግጦ ከእንቅልፉ ነቃ አልዋለም አላደረም ሀብቱን ንብረቱ፤ ቤቱን ጥሪቱን ሁሉ ሸጦ ለድሆች ሰጠ በዚህም አላበቃም ራሱን በባርነት ሸጦ ገንዘቡን ለድሆች መጸወተ፤ በዙዎች ሲያመሰግኑት ሲያደንቁት ውዳሴ ከንቱ ፈርቶ በገዳመ አስቄጥስ ከአባ መቃርስ ገዳም ገብቶ መነኮሰ በዚያም ለብዙ ዓመት በተጋድሎ ኖሮ በዛሬዋ ዕለት በክብር አረፈ። ኃጢያተኛ ተመልሶ በህይወት እንዲኖር እንጂ ሞቱን የማይሻ እግዚያብሔር ይመስገን፤ እኛንም ከአባ ጴጥሮስ በረከት ያሳትፈን።
No comments:
Post a Comment