Thursday, February 21, 2013

የካቲት 14



ዛሬ የካቲት 14  ቤተክርስቲያን  የሁለት አባቶችን መታሰቢያ አስባ ትውላለች፤ አንዱ አቡነ ቄርሎስ ነው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ የነበረ፤ በዚህ ስም የሚጠሩ ብዙ ቅዱሳን አሉ ታዋቂው ቂርሎስ አምደ ሃይማኖት የተባለው  ንስጥሮስን ተከራክሮ የረታው ነው እርሱ ሐምሌ 3 ነው መታሰቢያው፤ ዛሬ የምናከብረው ቂርሎስ ግን ከትውልድ አገሩ ከግብጽ  ወደ ኢትዮጵያ  መጣ በዚህም አቡነ ፊቅጦር ከተባለ ገዳም ለረጅም ዓመት በተጋድሎ ኖረ በኃላም የግብጽ ሊቃውንት ቅድስናውን ባዩ ጊዜ ሳይፈልግ በግዱ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ አድርገው ሾሙት እርሱም መንጋውን በፍቅር ጠብቆ በዛሬዋ ቀን በመልካም ሽምግልና አረፈ፤   ዳግመኛም በዛሬዋ ቀን የአንጾኪያው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሳዊሮስ አረፈ፤ ይህ አባት በልጅነቱ በየገዳማቱ እየዞረ አባቶችን ይጎበኝ ነበር፤ ከዕለታት በአንዱ ቀን ራቅ ወዳለ ገዳም ሄደ በዚያም ራሱን እስረኛ አድርጎ የሚኖር አንድ የበቃ ባህታዊ ጋር ደረሰ፤ ገና ከበሩ ሳለ "ሳዊሮስ አመጣጥህ መልካም ነው እነሆ የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳስ ትሆናለህ ህዝቡን በትምህርትህ ትጠብቃለህ መናፍቃንንም ወደ ቀናች ኃይማኖት ትመልሳለህ አለውስሜን እንዴት አወቀ ብሎ ደነገጠ ይላል፤ የዚህ ባህታዊ ትንቢት ተፈጽሞ አባ ሳዊሮስ ሊቀ ጳጳስ ሆነ በቅድስና በንጽሀና ህዝቡን አገለገለ ብዙዎችንም ወደ ቀናች ኃይማኖት መለሰ በዛሬዋ ቀንም በክብር አረፈ። የአባቶቻችን በረከት ይደርብን።

No comments:

Post a Comment