እነሆ የተባረከ የመጋቢት ወር ባተ ይህ ወር ልክ እንደ መስከረም ቀኑና ሌሊቱ እኩል 12 ሰዓት ነው ከዚህ በኃላ ግን ቀኑ እየጨመረ ይሄዳል። መጋቢት ወር እጅግ ታላላቅ የጌታችን የማዳኑ ስራ የተከናወነበት ወር ነው፤ ዓለም የተፈጠረው በዚህ ወር በሃያ ዘጠነኛው ቀን ነው፤ ጌታችን ጽንሰቱም በዚሁ ቀን ነው። ሆሳህና በ 22 ስቅለቱ በ 27 ትንሳኤው በ 29 ነው ይህ ታዲያ ጥንተ በዓሉ ነው፤ በኃላ ዘመን የተነሳው ዲሜጥሮስ ስቅለት ከዓርብ ሆሳህና፤ ደብረ ዘይት፤ ትንሴኤና ጰራቅሊጦስ እሁድን እንዳይለቁ ቀመር ከሰራ ባህረሐሳብን ካዘጋጀ በኃላ ቀናቱ የሚለያዩ ቢሆንም ቅሉ ጥንተ በዓላቱ ታስበው ይውላሉ። ይ...ህ የመጋቢት ወር ታላቁ አባት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስም ያረፉበት ወር ነው። የዲሜጥሮስ ቀመር እንዳለ ሆኖ አባቶቻችን ሌላም ስርዓት ሰሩ በዓቢይ ጾም ሀዘን እንጂ ደስታ የለምና የመጋቢት አቦን ለጥቅምት 5 የመጋቢት መድሐኒያለምን ለጥቅምት 27 እንዲሁም የመጋቢት ጽንሰቱን ለታህሳስ 22 ቀን አዙረው እንዲከበር አደረጉ፤ ዛሬ መጋቢት 1 ቀን በምድር ላይ ረጅም ዓመት የኖረው የሄኖክ ልጅ ማቱሳላ አረፈ፤ ዕድሜው 969 ነው ዘፍ 5፤27። እርሱም ቢሆን አንድ ቀን አልኖረም 1000 ዓመት በጌታ ዘንድ አንድ ቀን ናትና፤ ስለዚህም በምድር ላይ አንድ ቀን የኖረ ሰው የለም አይኖርምም ምነዋ ቢባል፤ የጌታችን ቃል አይሻርምና "ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህ" ዘፍ 2፤17 ስለዚህም አንድ ቀን ሳይኖር ሰው ይሞታል ። ከአባቶቻችን በረከት ያሳትፈን።
ቃለ ህይወት ያሰማልን
ReplyDelete