የካቲት 15
በዚህች ቀን የበራክዩ ልጅ ነብዩ ዘካርያስ አረፈ፤ ቁጥሩ ከደቂቀ ነብያት ነው፤ ብዙ ትንቢቶችን ተናግሯል ስለ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ስቅለት ዘካ 12፤10 የወጉትን ያዩታል አለ፤ ዳግመኛም ስለ ሆሳህና እንዲህ አለ "ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል፤" ዘካ 9፤9 ስለደብረዘይት ዳግም ምጽአትም ተናግሯል ዘካ 14፤5። ይሁዳ ክርስቶስን በ 30 ብር እንደሚሸጠው ዘካ 11፤12። ይህ ነብይ ደግሞ ስለ ጾም እንዲህ ሲል ተናግሯል "የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። የአራ...ተኛው ወር ጾም የአምስተኛውም የሰባተኛውም የአሥረኛውም ወር ጾም ለይሁዳ ቤት ደስታና ተድላ የሐሤትም በዓላት ይሆናል፤ ስለዚህም እውነትንና ሰላምን ውደዱ።" ዘካ 8፤19 ሌሎች ብዙ ትንቢቶችን ተናገረ፤ ትንቢት የሚናገርበት ወራት ሲፈጸም የካቲት 15 በዛሬዋ ቀን አንቀላፋ በአባቶቹ ነብያት መቃብርም ቀበሩት። በረከቱ ይደርብን።
"በአሕዛብም መካከል ብዘራቸው እንኳ በሩቅ አገር ሳሉ ያስቡኛል፥ ከልጆቻቸውም ጋር በሕይወት ይኖራሉ፥ ይመለሱማል።" ዘካ 10፤9 አሜን በስደት ያሉ ኢትዮጰያውያን ወገኖቻችንን ይመልስልን።
No comments:
Post a Comment