ጾም ማለት ሰውን ከምግብ መከልከል ነው፡፡ ፍት.አን.15 “ጾምሰ ተከልኦተ ብዕሊ ዕምመብልዕ በጊዜ እውቅ” ጾም ማለት በታወቀው ዕለት በታወቀው ሰዓት ሰው ከምግብ የሚከለከለው መከልከል ነው፡፡ መብል መጠጥ የኀጢአት መሠረት ነው በመብል ምክንያት ሞት በሰው ልጆች ላይ መጣ “ይችን ዕፀ በለስ ብትበሉ ሞትን ትሞታላችሁ” ዘፍ.2፥17 ጾም ማለት ሰውነት ከሚፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ መከልከል ወይም ለሰውነት የሚያምረውን የሚያስጐመዥውን ነገር መተው ማለት ነው፡፡
መብል መጠጥ ከልክ ሲያልፍ ከተዘወተረም ከእግዚአብሔር ይለያል፤ “ያዕቆብ በላ ጠገበ ወፈረ ገዘፈ ደነደነ ፈጣሪው እግዚአብሔርን ተወ ሕይወቱ ከእግዚአብሔር ተለየ” ዘዳ.32፥15-17 “የእግዚአብሔር መንግሥት መብልና መጠጥን አትሰብክም” ሮሜ.14፥16፣ 1ቆሮ.8፥8-13 “ዛሬ የሚራቡ የሚጠሙ ብፁአን ናቸው ይጠግባሉና ማቴ.5፥6 ጾም የሥጋ መቅጫ ነው፤ “ነፍሴን /ሰውነቴን/ በጾም ቀጣኋት መዝ.68፥10 ጾም በነቢያት የተመሠረተ በክርስቶስ የጸና በሐዋርያትም የተሰበከና የተረጋገጠ ለክርስቲያኖች ዲያብሎስን ድል የምንነሣበት መንፈሳዊ የጦር ዕቃ ነው፡፡ ስለዚህ ሐዋርያዊትና ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እንደምታስተምረን ይህን ጾም ከምግብ ለመከልከል ጋር ጸሎትን፥ ስግደትን፥ ምጽዋትንና የንስሐ ዕንባን ጨምረን እንጹመው፡፡ ጌታችንና ነቢያት፣ ሐዋርያት የተውልን መንፈሳዊ መሣሪያ ነውና፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ጾም የጾመው ለአብነት፣ ለማስተማር፣ ለአርዓያ ነው፡፡ በዚህ ታላቅ ጾም ጥንተ ጠላታችን ዲያብሎስ፣ ከሰው የሥጋ ጠባይ የሚመጣ ስስትና ፍቅረ ንዋይ ድል የተነሱበት ነው፡፡ እኛም ይህን እያሰብን በተለያየ መንገድ የሚመጣብንን ፈተና ለማራቅ ከዚህ ታላቅ ጾም በረከት እንድናገኝ እንጾማለን፡፡ ጸልዮ ጸልዩ፣ ጾሞ ጹሙ ብሎናል፡፡ ማቴ.6-16፡፡ ስለዚህም ትእዛዙን ለማክበር እንጾማለን፡፡
የዚህ ታላቅ ጾም ስያሜዎች፡-
1. ዐቢይ ጾም
የባሕርይ አምላክ በሆነዉ በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተመሠረተ በመሆኑ ዐቢይ ወይም ታላቅ ጾም ይባላል፡፡
2. ጾመ ሁዳዴ
በጥንት ጊዜ ገባሮች ለባለ ርስት የሚያርሱት መሬት ሁዳዴ ተብሎ ይጠራ ነበር፡፡ እኛም ባለቤቱ ኢየሱስ ክርስቶስን እያሰብን የምንጾመው በመሆኑ ጾመ ሁዳዴ ተብሏል፡፡
3. የካሳ ጾም
አዳምና ሔዋን ከገነት የተባረሩት ለውርደት ሞት ለሲዖል ባርነት የበቁት በመብል ምክንያት ነው፡፡ በመብል ምክንያት የሞተውን የሰው ልጅ ጌታችን በፈቃዱ በፈጸመው ጾም ካሰው፤ መንፈሳዊ ረሃብን በረሃቡ ካሰለት፡፡ ስለዚህም የካሳ ጾም ተባለ፡፡
4. የድል ጾም
አርዕስተ ኃጣውእ /ማቴ. 4/ ድል የተነሱበት በመሆኑ የድል ጾም ተብሏል፡፡
5. የመሸጋገሪያ ጾም
ጌታችን ከሕገ ኦሪት ወደ ሕገ ወንጌል ሊያሸጋግረን የጾመው ጾም በመሆኑ የመሸጋገሪያ ጾም ተብሏል፡፡
6. ጾመ አስተምህሮ
ጌታችን የጾመው ለትምህርት ነው፡፡ እርሱ መጾም ያለበት ሆኖ አይደለም፡፡ ስለዚህም ይህ ጾም ጾመ አስተምህሮ ይባላል፡፡ አርባ መአልትና አርባ ሌሊት ጾመ ማቴ.4፥2
7. የቀድሶተ ገዳም ጾም
ጌታችን ከከተማ ርቆ ከሰው ተለይቶ በመጾም ከከተማ ርቆ ከሰው ተለይቶ በብሕትውና መኖርን ቀድሶ የሰጠበት፣ የመጥምቁ ዮሐንስና የነቢዩ ኤልያስን ገዳማዊነት የባረከበት በመሆኑ የቀድሶተ ገዳም ጾም ተብሏል፡፡
8. የመዘጋጃ ጾም
ሕዝበ እሥራኤል የፋሲካውን በግ ከመመገባቸው በፊት ዝግጅት ያደርጉ ነበር፡፡ እኛም ትንሣኤን ከማክበራችን፣ ሥጋና ደሙን ከመቀበላችን በፊት በጾምና በጸሎት ዝግጅት የምናደርግበት በመሆኑ የመዘጋጃ ጾም ተብሏል፡፡
ዓቢይ ጾም ስምንት ሳምንት ማለትም 55 ቀናት አሉት፡፡ ከእነዚህም ቀናት ውሰጥ ሰባት ቅዳሜና ስምንት እሑዶች ይገኛሉ፡፡ አሥራ አምስት ቀናት ማለት ነው፡፡ እነዚህ ከጥሉላት እንጂ ከእህል ውኃ ስለማይጾሙ የሙሉ ቀናት ጾም አርባ ቀናት ብቻ ናቸዉ፡
የመጀመሪያው ሳምንት «ዘወረደ»
ማለት
በቀጥታ፣
ቃል
በቃል
ሲተረጐም
«የወረደ» ማለት
ነው፡፡
ይህም
በምስጢሩ
አምላክ
ወልደ
አምላክ
ጌታችን
ኢየሱስ
ክርስቶስ
ለቤዛ
ዓለም
በቅዱስ
ፈቃዱ
ሰው
ሆኖ
ከሰማየ
ሰማያት ከባሕርይ ልዕልናው
በትሕትና
ወርዶ
ከቅድስት
ድንግል
ማርያም
መወለዱን
የሚያመላክት፣
ይህም
የሚታወስበት፣
የሚወሳበት
የዐቢይ
ጾም
አንደኛው
ሳምንት
ነው፡፡
ዮሐ.3ዕ13፡፡
በጾምነቱ
ግን
ለዐቢይ
ጾም
መግቢያ
ሆኖ
ታላቅ
ገድልና
ድል
የተገኘበት
ጾመ
«ሕርቃል» ተብሎ
ይጠራል፡፡
ሕርቃል በ614
ዓ.ም
የቢዛንታይን
ንጉሥ
ነበር፡፡
ይህ
ሳምንት
በስሙ
የተጠራበትም
ምክንያት
በዘመኑ
ፋርሶች
ኢየሩሳሌምን
ወርረው
የጌታን
መስቀል
ማርከው
ወስደው
ነበር፡፡
ምእመናን
«ተዋግተህ
አስመልስልን» አሉት፡፡
እርሱም
«ሐዋርያት
ነፍስ
የገደለ
መላ
ዘመኑን
ይጹም
ብለዋል፡፡
ስለዚህ
ይኽንን
የዕድሜ
ልክ
ጾም
ፈርቼ
እንጂ
ደስ
ይለኛል» ሲል
መለሰላቸው፡፡
እነርሱም
«የአንድ
ሰው
ዕድሜ
ቢኖር
ሰባ
ሰማኒያ
ዘመን
ነው፡፡
እኛ
ተካፍለን
እንጾምልሃለን» ስላሉት
ፋርስ
ዘምቶ
መስቀሉን
ከእነዚያ
ነጥቆ
ይዞ
ወደ
ኢየሩሳሌም
ተመልሷል፡፡
መታሰቢያም
እንዲሆን
ይህን
የጾም
ሳምንት
በቀኖና
ውስጥ
አስገቡት፡፡
የመጀመሪያው ሳምንት ጾሙም
ጾመ
ሕርቃል
ይባላል፡፡
ታሪኩ
የመስቀል
ፍቅር
የተገለጠበት
ታሪክ
ነው፡፡
መዋዕለ ጾሙን በሰላመ ያስፈጽመን
source : http://www.eotc-mkidusan.org/
No comments:
Post a Comment