የካቲት 30
"እውነት እላችኋለሁ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም፤" ማቴ 11፤11። ዛሬ የካቲት 30 የከበረች የመጥምቁ ዮሐንስ ራስ ተገለጸችበት ቀን ነው ። ሄሮድስ አንገቱን ለአንዲት ጋለሞታ ዘፈኝ ሲል አስቆረጠው፤ ማር 6፤27። በዚህን ጊዜ ጣፋጭ መዓዛ አካባቢውን አወደው በዚህም ብዙ ድውያን ተፈወሱ ይላል። የተፍጻሚተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስን አንገቱን ሲቆርጡት ለሁለት ሰዓት አንገቱ አየር ላይ ቀጥ ብላ ቆመች ይላል፤ ግሩም ነው፤ ቅዱስ ጳውሎስ በጥላው ድውያን ይፈውስ ነበር፤ ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ በሰውነቱ መዓዛ የሚገርም ነው ። ከዚህ በኃላ በወጪት አድርጎ ለወለተ ሄሮዲያዳ ሰጣት የቅዱስ ...ዮሐንስ አንገት ክንፍ አውጥታ በረረች በደቡብ ዓረቢያ አስራ አምስት ዓመት ወንጌልን ሰበከች ሚያዚያ 15 ቀን አረፈች፤ ከዘመናት በኃላ ነጋዴዎች እዚያ ቦታ አደሩ ከነዚህም ሁለቱ ደጋግ ክርስቲያኖች ነበሩበት ቅዱስ ዮሐንስ በህልማቸው ተገለጸላቸው የከበረች እራሱንም እንዲያወጡ ነገራቸው ሲነጋም እንዳዘዛቸው አደረጉ ይህም የካቲት 30 ቀን ነው፤ ከቀሪ ስጋው ጋር ቀበሩት ቀድሞ ስጋው የተቀበረው በታላቁ ነብይ በኤልሳ መቃብር ነበር፤ ቅዱስ ዮሐንስ ሰኔ 30 ልደቱ ነው፤መስከረም 2 አንገቱ የተቆረጠበት ሚያዚያ 15 ያረፈበት፤የካቲት 30 ራሱ የተገለጸበት ነው። ከነዚህ ውስጥ መስከረም 2 እና ሰኔ 30ን ቤተክርስቲያን ሰማዕቱን በደማቁ ታዘክረዋለች። ከቅዱስ ዮሐንስ በረከት ያሳትፈን።
(ስንክሳር፤ገድለ ዮሐንስ መጥምቅ የካቲት ወር የሚነበብ)
No comments:
Post a Comment