በዚህች ቀን የእመቤታችን ጠባቂ፤ የስደት የመከራዋ ተካፋይ የነበረው ጻድቁ ዮሴፍ አረጋዊ አረፈ፤ ይህ ጻድቅ በመዲናችን አዲስ አበባ በስሙ በታነጸለት ቤተክርስቲያን በደማቁ ተከብሮ ይውላል ፤ አረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ ትዉልዱ በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 1፡15-16 ላይ እንደተገለጸዉ ፡- አዛርያ ማትያንና ቅስራን ይወልዳል፡፡ ማታንም ያዕቆብን ወለደ ፡፡ ያዕቆብ ክርስቶስ የተባለዉን ኢየሱስን የወለደች የማርያምን እጮኛ ዮሴፍን ወለደ፡፡ ቅስራ ደግሞ የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያም አባተ እያቄምን ወለደ፡፡ እያቄም ድንግል ማርያምን ወለደ፡፡ በዚህ ትዉልድ ሐረግ መሰረት እመቤታችን ማርያምና ቅዱስ ዮሴፍ በሦስት ቤት ዘመዳማቾች ናቸዉ ፡፡ቅዱስ ማቴዎስ ወንጌሉን ሲጽፍ በእመቤታችን ትዉልድ ያልቆጠረበት ምክንያት በአይሁድ ህግ ሴት ልጅ በዘር ሐረግ ስለማትቆጠር እመቤታችን እንዳትቀርበት ፈልጎ በእጮኛዋ በዮሴፍ በኩል ቆጥሯታል፡፡
ቅዱስ ዮሴፍ ለእመቤታችን የታጨበት ምክንያት
1-ኃይል አርያማዊት እንዳትባል (በመንፈስ ቅዱስ ስለጸለሰች )ኢሳ ፡1፡10
2-ፅንሱን ከአጋንት ለመሰወር (አጋንት ቢያዉቁ ብዙ ፅንስ ባበላሹ ነበርና)
3-ከርስት ገብቶ ሊቆጠርላት (በአይሁድ ህግ ዘር የሚቆጠረዉ በወንድ ነዉና) ማቴ 1፡16 ፣ ሉቃ 2፤4
4-በስደቷ ግዜ ሊላላካት ሊጠብቃት
5-ከዉግረት ሊያድናት (ባል የሌላት ሴት በኦሪት ህግ ፀንሳ ከተገኘች ትወገር ነበርና ዮሴፍ ባይኖር በድንጋይ ወግረን እንግደላት ይሉ ነበርና፡) በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር ባወቀ ቅዱስ ዮሴፍ ታጨላት፡፡ ዘሁ 5፡19
በማቴዎስ ወንጌል 1፡18-20‹‹ እመቤታችን ለዮሴፍ በታጨች ግዜ ሳይገናኙ በመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች፡፡እጮኛዋ ዮሴፍ ጻድቆ ሆኖ ሊገልጣት ስላልወደደ በስዉር ሊተዋት አሰበ››፡፡ ቅዱስ ዮሴፍ ጻድቅ ስለነበር ከማን ፀነስሽ ብሎ ቢጠይቃት በመንፈስ ቅዱስ ብላዋለች ፡፡መልአኩም በህልም ቢነግረዉ ቢረቅበት ግር ቢለዉ ነብያት ትንቢት የተናግሩለት ጌታ እንደ ፀነሰች፣ድንግልም የተባለች እሷእንደሆነች ስላላወቀ ሐዋርያዉ ሲጽፍ ‹‹የበኩር ልጅዋን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም አለ›› ማቴ 1፡25 ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ አገላለጽ‹‹‹ እስከ ›››የሚለዉ ቃል መጨረሻ የሌለዉ እስከ ነዉ ፡፡ዘፍ 8፡7 ‹‹ቁራ ዉኃዉ እስኪድርቅ ድረስ….››ከደረቀም በኃላ አልተመለሰም ፡፡ 1ኛ ሳሙ 6፡23 ‹‹ሜልኮም እስከሞተችበት ቀን ድረስ ልጅ አልወለደችም ››ይላል ከሞተች በኃላ ልጅ ወለደች ማለቱ እንዳልሆነ ሁሉ ቃሉ የሚያስረዳዉ መጨረሻ የሌለዉ እስከ ነዉ፡፡ቅዱስ ዮሴፍ በኃላ ግን በቤተልሔም አምስት ነገር አይቶ አምኗል ትንቢቱም እንደተፈጸመ አዉቋል፡፡ እምስቱ ነገርም
1- የእግዚአብሔር ክብሩን ብርሃኑን በቤተልሔም አይቶ ፣
2-ኮከብ ከምስራቅ ወጥቶ ወደ መስብ በመሄዱ ፣
3-የሰብአ ሰገል በክብር በስጦታ ከሩቅ ሀገር መጥተዉ ሲገብሩለተት በማየቱ ፣
4- የእረኞች መፍራት መደንገጥ ሲመለከት ፣
5-ቅዳሴ መላእክት ምስጋና ስብሐተ እግዚአብሔር ሰዉና መላእክት በአንድላይ ሲዘምሩ በማየቱ ቅዱስ ዮሴፍ እመቤታችንን የአምላክ እናት እንደሆነች አወቀ፡፡ ፡፡ይቆየነ የቅዱስ ዮሴፍ በረከቱ ረድኤቱ ይደርበን አሜን፡፡
LIKE >>>
https://www.facebook.com/pages/ተዋህዶ-ሀይማኖታችን/117298008428339?ref=hl
ቃለ ሕይወት ያሰማልን። እግዚኣብሔር ያገልግሎት ዘመንህን ይባርክልህ. እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለዘልዓልም ትጠብቀን አሜን.
ReplyDelete