Thursday, July 4, 2013

ሰኔ 27


በዚህች ቀን ታሪኩ በሐዋርያት ስራ ምዕራፍ 910 ላይ የተጠቀሰው ሐዋርያው ሐናንያ አረፈ። ቀድሞ ሳኦል የተባለው ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ክርስቲያኖችን ሲያሳድድ ድንገት በደማስቆ ታላቅ ብርሃን ይመታዋል በምድር ይወድቃል ዓይኑም ይታወራል፤ ሳውል ሳውል ስለምን ታሳድደኛለህ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል ይለዋል፤ 3 ቀን 3 ሌሊት ዓይነስውር ሆኖ ይቆያል። ከዚያም የዛሬዋን ቀን መታሰቢያውን የምናደርግለት ሐዋርያው ሐናንያ እጁን ጭኖ ጸለየለት ዓይኑንም አበራለት ከዚያ በኃላ ነው ቅዱስ ጳውሎስ የቤተክርስቲያን ምርጥ እቃ የሆነው። ሐዋርያው ሐናንያ በደማስቆ ኤጲስቆጶስ አድርገው ሾሙት ወንጌልን ሰብ ብዙዎችን ወደቀናች ሀይማኖት መለሳቸው፤የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው ከዚህ በኃላ አረመኔው ንጉስ ሉክያኖስ ይዞ ብዙ መከራ አደረሰበት፤ አስገረፈው፤ በእሳት አቃጠለው፤ በፍላጻ አስነደፈው፤ በመጨረሻም በዛሬዋ ቀን በድንጋይ አስወግሮ ገድሎታል። ዳግመኛ በዛሬዋ ቀን ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በሉቃስ ወንጌል 1620 ታሪኩን የተናገረለት ዓልአዛር አረፈ። እንዲህ ይላል “… አልዓዛርም የሚባል አንድ ድሀ በቍስል ተወርሶ በደጁ ተኝቶ ነበር፥ ከባለ ጠጋውም ማዕድ ከሚወድቀው ፍርፋሪ ሊጠግብ ይመኝ ነበር፤ ውሾች እንኳ መጥተው ቍስሎቹን ይልሱ ነበር። ድሀውም ሞተ፥ መላእክትም ወደ አብርሃም እቅፍ ወሰዱት ይላል የዚህ ጻድቅ እረፍቱ ዛሬ ነው፤ ይህም ሰኔ 27 የሚነበበው ስንክሳር ላይ ተጽፏል።ለእግዚያብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም የአባቶቻችንን በረከት ያሳትፈን።

1 comment:

  1. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን!
    በመጀመሪያ መንፈሳዊ ሰላምታዬ ይድረስልኝ፡፡
    እስከሁን ከማያቸው ብሎጎችና ዌብ ሳይቶች ይህን ብሎግ እመርጣሉሁ፡ ዝግጅቱ ከየወራቱ ብዙ ቀናትን ስለሚዳስስ ነው፡፡ የእለት እንጀራ እጅግ በጣም ጥሩ ሲሆን ይዘቱ ግን በጣም እጥር ይላል፡፡ የዚህ ብሎግ ደግሞ ዝግጅቱ በጣም ጥሩ ሆኖ ሳለ
    1. ሁሉኑም ቀናት አይሸፍንም
    2. የሚቀርበውም ቀናቶቹ ካለፉ በኋላ ነው፡፡ ሲሆን አንድ ቀን ቀደም ብሎ ካልሆነም በእለቱ መቅረብ ነበረበት፡፡ ሕዝነን የበረከት ተሳታፊ ከማድረግ ታሪክ አንባቢ እያደረጋችሁት ነው፡፡
    እኛንም አንብቦ ለመጠቀም ያብቃን
    እናንተንም ታላላቅ አባቶቻችን የተቀበሉትን በረከት ተካፋይ ያድርጋችሁ!
    ሀገራችንና ሕዝበ ክርስቲያኑን ይማርልን!
    ማሳሰቢያ ጽሁፎቻችሀሁ የሆሄያት ህግን የጠበቁ ይሁኑ፡፡

    ReplyDelete