በዚህች ቀን ቅዱስ አባት ወንጌሉ ዘወርቅ የተባለ ዮሐንስ አረፈ፤አገሩ ሮሜ ነው ወላጆቹ በሀብት በዘመድ የከበሩ ናቸው፤አባቱ ያሰራለትን ገበታው የወርቅ የሆነ ወንጌል ይዞ ከቤት ጠፍቶ ገዳም ገባ ሰባት ዓመት በተጋድሎ ኖረ፤ ድጋሚ ወደ አገሩ ተመለሰ ምስኪን ደሃ መስሎ በአባቱ ደጅ ወድቆ የአባቱ አሽከሮች ትርፍራፊ እየጣሉለት ለብዙ ጊዜ በጽናት ኖረ፤አናቱ ስትገባ ስትወጣ የሚከረፋ ሽታው ያስጨነቃት ነበር። የእረፍት ቀኑ ሲደርስ እናትና አባቱን አስጠርቶ ልጃቸው እንደሆነ ገለጸላቸው ሲሞትም በለበሳት እራፊ ጨርቅ ብቻ እንዲገንዙት አምሏቸው በዛሬዋ ቀን አረፈ መሪር ለቅሶ አለቀሱለት ሮሜ ሁሉ አለቀሰች፤ ከስጋውም ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራት ተገለጹ። በረከቱ ይደርብን
No comments:
Post a Comment