Thursday, May 16, 2013

ግንቦት 7



በዚህች ቀን ታላቁ የቤተክርስቲያን ሊቅ አቡነ አትናቴዎስ አረፈ። ወላጆቹ አረማውያን ነበሩ ያላመኑ ያልተጠመቁ የአባቱ ስም ሐኪም የእናቱ ስም ማርያም ይባላል መስከረም 20 ቀን ነው የተወለደው። አትናቲዎስ ህጻን እያለ የሰፈሩ ልጆች ደስ የሚል ጨዋታ ሲጫወቱ ይመለከታል ለመሆኑ እንዴት ያለ ጨዋታ ነበር ካሉ እንደ ዘመናችን ህጻናት ሌባና ፖሊስ፤ ...ባሮሽ፤ ኳስ፤ ወይንም እርግጫአልነበረም፤ ስርዓተ ቤተክርስቲያን እየሰሩ ነበር የሚጫወቱት፤ እትናቴዎስ እኔንም ከጫወታችሁ አስገቡኝ አላቸው እነሱም አንተ ያልተጠመቅህ አረማዊ ነህ ከጫወታችን አትገባም አሉት እሺ አጥምቁኝና አስገቡኝ ሲላቸው የጫወታ ጥምቀት አጠመቁት የጫወታ ሊቀ ጳጳስ አድርገው ሾሙትና ወንበር ላይ አስቀመጡት ሰገዱለት በዚያን ወራት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ የነበረው እለእስክንድሮስ ነው ደቀመዛሙርቱን አስከትሎ መንገድ ሲሄድ የእነዚህ ህጻናትን ጫወታ በመገረም ቆሞ ተመለከተ፤አባታችን ከነዚህ ህጻናት ምን ቁም ነገር ይገኛል ብለህ ትመለከታቸዋልህ አሉት፤እርሱም ይገኛል እንጂ ልጆቼ እነዚህ ህጻናት ያደረጉት በኃለኛው ዘመን እግዚያብሔር በእኔ ላይ አድሮ የሚሰራው ስርዓት ነው፤እነሆ በግብጽ ምድር ጽኑ ርሀብ ይከሰታል የዚህ ህጻን አባቱ ይሞታል እናቱም እንዳሳድገው አምጥታ ለእኔ ትሰጠኛለች ከእኔ በኃላ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ የሚሆነው ይህ ህጻን ነው ብሎ ትንቢት ተናገረለት፤ እንዳለውም ሆነ አባቱ ሲሞት እናቱ ቢኖርም ቢሞትም ከዚህ በኃላ አባቱ አንተ ነህ ብላ አደራ ሰጠችው፤እርሱም በመልካም ስነ ምግባር አሳደገው ዲቁና ቅስና ሾመው በኃላም እርሱ ሲሞት 20ኛው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ እድርገው ሾመውታል፤ በዚህ በሹመቱ ወራት ብዙ ድርሳናትን ተግሳጻትን መልዕክታትን ጽፏል፤ ግሩም ቅዳሴም ደርሷል፤ እንዲያውም በዛሬዋ ቀን አብዛኞቹ አብያተክርስቲያናት ቅዳሴ እትናቴዎስን ነው የሚቀደሰው፤ እንዴት ያለ ግሩም ቅዳሴ ነው/// በነገራችን ላይ አቡነ አትናቴዎስ የመጀመሪያውን የኢትዮጰያን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃንን ቀብቶ የሾመ አባት ነው፤ይህ ታሪክ ደግሞ በሁለተኛ ደረጃና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ደረጃ የታሪክ ትምህርት ካሪኩለም ውስጥ የተካተተ ነው። አቡነ አትናቴዎስ 318 ሊቃውን በኒቂያ ጉባዬ አርዮስን ተከራክረው ሲረቱ አፈጉባዬ የነበረ አባት ነው፤ ልክ እንደ ዲዮስቆሮስ በደሴተ ጋግራን ለሰባት ዓመት በግዞት ኖሯል፤ይህን አባት የማይጠቅሰው ሊቅ የለም፤ ሃይማኖተ አበው ላይ በስፋት ይገኛል፤ ሊቀ ጳጳስ ሆኖ 46 ዓመት ህዝቡን በፍቅር ካገለገለ በኃላ ግንቦት 7 ቀን በክብር አርፏል፤ በረከቱ ይደርብን

No comments:

Post a Comment